From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ
ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x)
ማን ፡ ጠርቶ ፡ አፈረብህ ፡ አንገቱን ፡ ደፋብህ
ቀና ፡ አልልም ፡ ብሎ ፡ ተሸማቀቀብህ
እኔስ ፡ አላየሁም ፡ ከቶ ፡ አልሰማሁም
ከፍ ፡ ከፍ ፡ አልኩ ፡ አንጂ ፡ አላሽቆለቆልኩም
ሲወራ ፡ ሰምቼ ፡ ነበረ ፡ አሁን ፡ ግን ፡ ዓይኔ ፡ አይቷል
ምሥጋናዬም ፡ ብሷል
አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ
ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x)
እርሱማ ፡ ሞኝ ፡ ነው ፡ ጊዜውን ፡ ይፈጃል
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲል ፡ ዕድሜውን ፡ ይገፋል
ቢሉኝ ፡ ከሰነፎች ፡ መንደር ፡ አንዳንዶቹ
እንግዲህ ፡ ማዳኑን ፡ ያያል ፡ ዓይናቹህ
በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ ፡ በሰማይ ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት
አለኝ ፡ በኢየሱስ ፡ ቤት
አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ
ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x)
ሞቅ ፡ ደመቅ ፡ ካሉ ፡ ከፈርዖን ፡ ቤት
በንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ስልጣን ፡ ካለበት
ጮማ ፡ ሲል ፡ ወይን ፡ ጠጅ ፡ ድሎት ፡ በሞላበት
ብድራቱን ፡ ቆጥሮ ፡ ሙሴ ፡ አድርጓል ፡ ለቀቅ
ለሁሉ ፡ እንደስራው ፡ ምትከፍል ፡ ነህና ፡ አምላኬ
አረፈብህ ፡ ልቤ
አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ
ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x)
እርሱማ ፡ ሞኝ ፡ ነው ፡ ጊዜውን ፡ ይፈጃል
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲል ፡ ዕድሜውን ፡ ይገፋል
ቢሉኝ ፡ ከሰነፎች ፡ መንደር ፡ አንዳንዶቹ
እንግዲህ ፡ ማዳኑን ፡ ያያል ፡ ዓይናቹህ
በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ ፡ በሰማይ ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት
አለኝ ፡ በኢየሱስ ፡ ቤት
አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ
ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x)
ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x)
ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x)
|