አባናና ፡ ፋርፋ (Abanana Farfa) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 1.jpg


(1)

የወንጌል ፡ አርበኛ
(Yewengiel Arbegna)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ መድሃኒት ፡ ነው
እርሱን ፡ ይዤ ፡ አሰቃዬን ፡ ከየት ፡ ላገኘው (፪x)
የለም ፡ አጣሁት ፡ የለም ፣ የለም ፡ ፈለኩት ፡ የለም
ጌታዬ ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም ፣ ኢየሱሴ ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም

ይፈውሳል ፡ ሲባል ፡ ሰማሁና ፡ ፈጥኜ ፡ ከቤቱ ፡ መጣሁና
ቃሌን ፡ አድርግ ፡ ብሎ ፡ ተዕዛዝ ፡ ሲያዘኝ
የመዳኔን ፡ መንገድ ፡ ሲጠቁመኝ
አላልኩም ፡ አባናና ፡ ፋርፋ ፣ አልሄድኩም ፡ ወደዚያ ፡ ልጠፋ (፪x)

አልቻልኩትም ፡ ብሎ ፡ አልጻፈም ፡ መሸኚያ (አሃሃሃ ፡ ሃሃ ፡ ሃሃሃ)
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የፈውሴ ፡ መገኛ (አሃሃሃ ፡ ሃሃ ፡ ሃሃሃ) (፪x)

ባለመድሃኒት ፡ መድሃኒተኛ (፬x)

የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ መድሃኒት ፡ ነው
እርሱን ፡ ይዤ ፡ አሰቃዬን ፡ ከየት ፡ ላገኘው (፪x)
የለም ፡ አጣሁት ፡ የለም ፣ የለም ፡ ፈለኩት ፡ የለም
ጌታዬ ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም ፣ ኢየሱሴ ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም

ከኖርኩበት ፡ መንደር ፡ በድንገት ፡ ወጥቼ
የጠፋውን ፡ ነገር ፡ ፈልጌ ፡ አጥቼ
የልቤን ፡ መሻት ፡ ቢነግረኝ ፡ አልኩና
ከኢየሱሴ ፡ መንደር ፡ ድንገት ፡ ብቅ ፡ አልኩና
አላሰብኩም ፡ አልገመትኩም ፡ የሆነልኝ ፡ ነገር
ሲያንስበት ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ መዘመር

ይፈውሳል ፡ ሲባል ፡ ሰማሁና ፣ ፈጥኜ ፡ ከቤቱ ፡ መጣሁና
ቃሌን ፡ አድርግ ፡ ብሎ ፡ ተዕዛዝ ፡ ሲያዘኝ
የመዳኔን ፡ መንገድ ፡ ሲጠቁመኝ
አላልኩም ፡ አባናና ፡ ፋርፋ ፣ አልሄድኩም ፡ ወደዚያ ፡ ልጠፋ (፪x)

አልቻልኩትም ፡ ብሎ ፡ አልጻፈም ፡ መሸኚያ (አሃሃሃ ፡ ሃሃ ፡ ሃሃሃ)
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የፈውሴ ፡ መገኛ (አሃሃሃ ፡ ሃሃ ፡ ሃሃሃ) (፪x)

ባለመድሃኒት ፡ መድሃኒተኛ (፬x)

የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ መድሃኒት ፡ ነው
እርሱን ፡ ይዤ ፡ አሰቃዬን ፡ ከየት ፡ ላገኘው
(፪x)
የለም ፡ አጣሁት ፡ የለም ፣ የለም ፡ ፈለኩት ፡ የለም
ጌታዬ ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም ፣ ኢየሱሴ ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም