ይቤዠኛል (Yebezegnal) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ሰው ፡ ከሆነበት ፡ አስደንጋጭ ፡ ወሬ
ወየው ፡ ከሚያሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ፍሬን ፡ አሄ
ሳልርበተበት ፡ ሳልል ፡ የት ፡ ልግባ
ከዓይኔ ፡ ሳይወጣ ፡ የሃዘን ፡ እንባ

አዝ፦ ይቤዠኛል ፡ ያልኩት ፡ ይቤዠኛል
ያድነኛል ፡ ያልኩት ፡ ያድነኛል (፪x)

ነፍሴ ፡ ማን ፡ አለና ፡ የቱን ፡ ለማን ፡ ስትል
ድንገት ፡ ስታጣቸው ፡ ቃል ፡ የገቡላትን
እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ አቅፎ ፡ የተቀበላት
በጣም ፡ በጭንቋ ፡ ቀን ፡ አላት ፡ የሚቤዣት (፪x)

አዝ፦ ይቤዠኛል ፡ ያልኩት ፡ ይቤዠኛል
ያድነኛል ፡ ያልኩት ፡ ያድነኛል (፪x)

እተርፋለሁ ፡ አላልቅም ፡ አብሬ
የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በመንደሬ
የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በሰፈሬ
ለኃጢአተኛው ፡ የሚመጣው ፡ ዱላ
የጻድቁን ፡ ቤት ፡ አይነካምና
የመንፈሱን ፡ ቤት ፡ አይነካምና

እሩትን ፡ ከተቤዣት ፡ ከቡሄዝ ፡ በልጦ
ለተሻለው ፡ ኪዳን ፡ ለእኔ ፡ ዋስ ፡ የሆነው
ልቤን ፡ የጣልኩበት ፡ ጌታ
በጭንቄ ፡ ደራሽ ፡ ነው ፡ ሚያስመካ (፪x)

እተርፋለሁ ፡ አላልቅም ፡ አብሬ
የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በመንደሬ
የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በሰፈሬ
ለኃጢአተኛው ፡ የሚመጣው ፡ ዱላ
የጻድቁን ፡ ቤት ፡ አይነካምና
የመንፈሱን ፡ ቤት ፡ አይነካምና

አዝ፦ ይቤዠኛል ፡ ያልኩት ፡ ይቤዠኛል
ያድነኛል ፡ ያልኩት ፡ ያድነኛል (፪x)