From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በሰነፍ ፡ ምክር ፡ ልቡ ፡ ተውጦ
የጽድቅን ፡ መንገድ ፡ የሄደ ፡ አቋርጦ
የሥጋን ፡ ለባሽ ፡ ደጅ ፡ እየጠና
ዛሬም ፡ ይኖራል ፡ ሆኖ ፡ ጥገኛ
ያ ፡ ሰው ፡ ያ ፡ ሰው
ፊቱን ፡ ብፈልግ ፡ ደጁን ፡ ብጠና
ኧረ ፡ አትዘን ፡ ብሎ ፡ ያረገኝ ፡ ቀና
ዛሬም ፡ የሙጥኝ ፡ እርሱን ፡ እላለሁ
የእኔስ ፡ ደጋፊ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ካለው ፡ ተወለድ ፡ ወይ ፡ ካለው ፡ ተጠጋ
የሚለው ፡ ተረት ፡ መች ፡ ይገባኛል
ኢየሱስ ፡ ካለኝ ፡ ሁሉም ፡ እንዳለኝ ፡ መንፈስ ፡ ነግሮኛል
በሰው ፡ የወጣ ፡ በሰው ፡ ይወርዳል
የተሰጠውም ፡ በመንገድ ፡ ያልቃል
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ ምንጭን ፡ ያፈልቃል
(ስሙኝማ) ፡ የእኔ ፡ ደጋፊ
(ስሙኝማ) ፡ ካለልኝ ፡ ከጐኔ
(ስሙኝማ) ፡ ማንም ፡ ሰው ፡ ባይኖረኝ
(ስሙኝማ) ፡ ምን ፡ ሊጨንቀኝ ፡ እኔ
ሁሉን ፡ የሚያስንቅ ፡ በልጦ ፡ ሚተካ
የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ አለለኝ ፡ ጌታ
አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ
አለልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ አለልኝ
በልምምጥ ፡ ቃል ፡ በአባባይ ፡ ቋንቋ ፡ ተቀለጣጥፎ ፡ ሰው ፡ የተጠጋ
ፍጻሜ ፡ ሳይደርስ ፡ አንገቱን ፡ ደፍቶ ፡ ቆሟል ፡ እዛጋ
የአምላኩን ፡ ፊት ፡ እየፈለገ
ጌታን ፡ በመፍራት ፡ ተግቶ ፡ የኖረ
ላይቆም ፡ ይሄዳል ፡ የጌታን ፡ ማዳን ፡ እየሰበከ
ዘንድሮ ፡ ሆኗል ፡ ምላስ ፡ ላላቸው
የሰው ፡ ደጋፊ ፡ ለበዛላቸው
ብለው ፡ ለሚሉ ፡ ጌታ ፡ ልኮኛል ፡ እንዲህ ፡ እንድላቸው
እነ ፡ ኤልያብ ፡ ሰልፍ ፡ እንደያዙ
እኔን ፡ ብቀባኝ ፡ ብለው ፡ ሲጓጉ
ጌታ ፡ የደገፈው ፡ ዳዊት ፡ ተቀባ ፡ እነሱ ፡ እያዩ
(ስሙኝማ) ፡ የእኔ ፡ ደጋፊ
(ስሙኝማ) ፡ ካለልኝ ፡ ከጐኔ
(ስሙኝማ) ፡ ማንም ፡ ሰው ፡ ባይኖረኝ
(ስሙኝማ) ፡ ምን ፡ ሊጨንቀኝ ፡ እኔ
ሁሉን ፡ የሚያስንቅ ፡ በልጦ ፡ ሚተካ
የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ አለለኝ ፡ ጌታ
አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ
አለልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ አለልኝ
በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ዓይኑን ፡ የጣለ
አለኝ ፡ እከሌ ፡ ለሁሉ ፡ ያለ
የተመካበት ፡ ድንገት ፡ ሲሰበር ፡ ዓይኔ ፡ ይሄን ፡ አየ
ከዘመድ ፡ አዝማድ ፡ ዓይኑን ፡ ያነሳ
በአምላኩ ፡ ታምኑ ፡ ከዑር ፡ የወጣ
አንዱን ፡ ደጋፊ ፡ አብርሃም ፡ ይዞ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ አጣ
(ስሙኝማ) ፡ የእኔ ፡ ደጋፊ
(ስሙኝማ) ፡ ካለልኝ ፡ ከጐኔ
(ስሙኝማ) ፡ ማንም ፡ ሰው ፡ ባይኖረኝ
(ስሙኝማ) ፡ ምን ፡ ሊጨንቀኝ ፡ እኔ
ሁሉን ፡ የሚያስንቅ ፡ በልጦ ፡ ሚተካ
የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ አለለኝ ፡ ጌታ
አለልኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ
አለልኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ አለልኝ
|