ሳየው (Sayew) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ውስጤን ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ይለኛል ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ደስ (X ፪)
ምን ፡ ሆነህ ፡ ነው ፡ ካሉኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ማን ፡ አገኘህ ፡ ላሉኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ

    ሰላሜማ ፡ ደስታዬማ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ
    ምንም ፡ ነገር ፡ የማይተካው ፡ ነው ፡ የዘላለሜ
    (ሳየው ፡ ካጎነበስኩበት ፡ ሳየው ፡ ቀና ፡ ቀና ፡ እላለሁ
    ሳየው ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው ፡ ሳየው ፡ በፊቱ ፡ እዘላለሁ) ፡ X ፪
    ሳየው ፡ ሳየው ፡ ሳየው (፪)

ሁልጊዜ ፡ ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ የሚያውቁኝ
ሀዘኔ ፡ ተገፍፎ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ አገኙኝ
እጅጉን ፡ ተገርመው ፡ አይን ፡ አይኔን ፡ ፡ እያዩኝ
ምን ፡ ብታገኝ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ያለህ ፡ እያሉ

ብር ፡ ነው? ወርቅ ፡ ነው? ምስጢሩን ፡ ንገረን
እንዲህ ፡ መለወጥህ ፡ በጣም ፡ ነው ፡ የገረመን
በማለት ፡ ጥያቄ ፡ ለእኔ ፡ ሲያቀርቡ
ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ አንድ ፡ ነው ፡ ምስጢሩ

ኢየሱሱ ፡ እየሱስ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (X ፪)

    ሰላሜማ ፡ ደስታዬማ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ
    ምንም ፡ ነገር ፡ የማይተካው ፡ ነው ፡ የዘላለሜ
    (ሳየው ፡ ካጎነበስኩበት ፡ ሳየው ፡ ቀና ፡ ቀና ፡ እላለሁ
    ሳየው ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው ፡ በፊቱ ፡ እዘላለሁ) ፡ X ፪
    ሳየው ሳየው ሳየው ሳየው ፡ (X ፪)

ሰው ፡ አለኝ ፡ ቢለኝ ፡ የእርካታ ፡ ምንጭ
የደስታ ፡ ምንጭ ፡ ልክ ፡ ነው ፡ እሱማ
ከአምላኬ ፡ አይበልጥም ፡ አንጂ ፡ ከኢየሱስ ፡ አይበልጥም ፡ እንጂ (X ፫)