ቀስ ፡ ረጋ (Qes Rega) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

አዝ፦ ቀስ ፡ ረጋ ፡ ቀስ ፡ ረጋ
አለች ፡ ነፍሴ
ስላስመካት ፡ ኢየሱሴ (፪x)
አለሁ ፡ ሲላት ፡ ኢየሱሴ (፪x)

ባራቱም ፡ አቅጣጫ ፡ ልብ ፡ የሚያርድ ፡ ወሬ
ከፈሩቱ ፡ መንደር ፡ ደረሰው ፡ ጆሮዬ
ከላይ ፡ እንዳልሆነ ፡ ነፍሴ ፡ አረጋግጣ
ሁሉ ፡ ደህና ፡ ነው ፡ ሲል ፡ ቀስ ፡ በይ ፡ ሲላት ፡ ጌታ
ቀስ ፡ ረጋ

አዝ፦ ቀስ ፡ ረጋ ፡ ቀስ ፡ ረጋ
አለች ፡ ነፍሴ
ስላስመካት ፡ ኢየሱሴ (፪x)
አለሁ ፡ ሲላት ፡ ኢየሱሴ (፪x)

በሄድኩበት ፡ ቦታ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ያወራል
ነገ ፡ ምን ፡ ሊኮን ፡ ነው ፡ ምን ፡ ይሻላል ፡ ይላል
በፀሎቴ ፡ ሆኜ ፡ ጌታን ፡ ብጠይቀው
ልመጣ ፡ ስለሆነ ፡ አለኝ ፡ ምልክት ፡ ነው

የእኔስ ፡ ነፍስ ፡ ሰምታለች ፡ መረጃ ፡ ከእውነተኝው ፡ ጣቢያ
የእኔስ ፡ ነፍስ ፡ ስለምን ፡ ትረበሽ ፡ ወዮ ፡ ትበል ፡ ታድያ (፪x)

ያረጋጋት ፡ ጌታ ፡ አለላት
ያረጋጋት ፡ ውዷ ፡ አለላት (፪x)

አዝ፦ ቀስ ፡ ረጋ ፡ ቀስ ፡ ረጋ
አለች ፡ ነፍሴ
ስላስመካት ፡ ኢየሱሴ (፪x)
አለሁ ፡ ሲላት ፡ ኢየሱሴ (፪x)