መጽናኛዬ (Metsnagnayie) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

የልቤ ፡ አፅናኝ
አይዞህ ፡ ምትለኝ
ከሞት ፡ አውጥተኸኝ
ህያው ፡ ያረከኝ

አዝመፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ
መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ

በጣፋጩ ፡ ዜማ ፡ ቃላትን ፡ መርጬ
በመንፈስ ፡ ማደሪያ ፡ ወዳንተ ፡ ገብቼ
ይኸው ፡ ልቤ ፡ ይኸው ፡ ልቤ ፡ ላንተ ፡ ያለውን ፡ አክብሮት ፡ ይገልጣል
እንዲህ ፡ ይልሃል

አዝመፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ
መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ

ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
በጥላህ ፡ አርፌ ፡ ብያለሁኝ ፡ እፎይ
ከስትንፋስ ፡ የሚቀርብ ፡ የለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
የልቤ ፡ መበርቻ ፡ መፅናኛ ፡ ከለላ

የልቤ ፡ አፅናኝ
አይዞህ ፡ ምትለኝ
ከሞት ፡ አውጥተኸኝ
ህያው ፡ ያረከኝ

አዝመፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ
መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ

ካእላፋት ፡ መሀል ፡ እንዴት ፡ ትዝ ፡ እንዳልኩህ
ማን ፡ ሆኜ ፡ አዳንከኝ ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ ጠየኩህ
አንተም ፡ መለስክልኝ ፡ በጣፋጩ ፡ ቃልህ
ፍቅር ፡ እንደሆነ ፡ ለኔ ፡ ግድ ፡ ያስባለህ

በጣፋጩ ፡ ዜማ ፡ ቃላትን ፡ መርጬ
በመንፈስ ፡ ማደሪያ ፡ ወዳንተ ፡ ገብቼ
ይኸው ፡ ልቤ ፡ ይኸው ፡ ልቤ ፡ ለአንተ ፡ ያለውን ፡ አክብሮት ፡ ይገልጣል
እንዲህ ፡ ይልሃል

አዝመፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ
መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ