From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በግብፅ ፡ የነበረውን ፡ የህዝቡን ፡ ጩኸት ፡ የሰማ ፡ ጌታ
ጊዜና ፡ ዘመን ፡ ጠብቆ ፡ ወደኔ ፡ መጣ
በቃ ፡ አለው (፪x) ፡ ያን ፡ ክፉ
በቃ ፡ አለው ፡ ያን ፡ ክፉ
ጌታዬ ፡ ከልሎኝ ፡ በክንፉ (፬x)
ያቤቱታ ፡ ድምፄ ፡ ወደ ፡ ጆሮው ፡ ደርሶ
የምህረት ፡ ፊቱን ፡ ወደኔ ፡ መልሶ
ከጨቋኙ ፡ ገዢ ፡ ነፍሴን ፡ አላቋታል
ውስጤን ፡ በደስታ ፡ እንዲህ ፡ አስብሎታል ፡ አሄ
አስባለሁ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፪x)
እላለሁ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፪x)
በውርደቴ ፡ መንደር ፡ ክብር ፡ ያየሁበት
የቆሰለው ፡ ልቤ ፡ የተፈወሰበት (፪x)
እላለሁ ፡ እላለሁ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ የለም ፡ አሜን (፪x)
እንደ ፡ ወትሮው ፡ ሰላም ፡ አውለኝ ፡ ብዬ ፡ ስነሳ
የፈሮኦንን ፡ ጡብ ፡ ልሰራለት ፡ ከቤት ፡ ስወጣ
ያስገባሪዬን ፡ ገመድ ፡ ከላዬ ፡ ሊፈታልኝ
አምላኬ ፡ መጣ ፡ ያዘንኩበትን ፡ ቀን ፡ ቀጥሮልኝ
ግብፅን ፡ ለቅቄ ፡ ያን ፡ ቀን ፡ ስወጣ
ፈርኦን ፡ ሲያየኝ ፡ እንዲህ ፡ አልኩታ
ጉልበቴ (፪x)
ላዳነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
አትበላው ፡ ከሳሼ
በግብፅ ፡ የነበረውን ፡ የህዝቡን ፡ ጩኸት ፡ የሰማ ፡ ጌታ
ጊዜና ፡ ዘመን ፡ ጠብቆ ፡ ወደኔ ፡ መጣ
በቃ ፡ አለው (፪x) ፡ ያን ፡ ክፉ
በቃ ፡ አለው ፡ ያን ፡ ክፉ
ጌታዬ ፡ ከልሎኝ ፡ በክንፉ (፬x)
|