እጁ ፡ መጣ (Eju meta) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ቀን ፡ ተቀጥሮ ፡ ለመሞቴ
ሊያበቃ ፡ ይህ ፡ ታሪኬ
ጀንበር ፡ ልትጠልቅ ፡ አዘቅዝቃ
ያለኝ ፡ ተስፋ ፡ ሊያበቃ ፡ ሲል

እጁ ፡ መጣ (፬x)
ጌታ ፡ መጣ (፬x)
እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x)

ለብዙ ፡ ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ ጦር ፡ ከጁ ፡ ያልተለየው
ወርውሮ ፡ ወርውሮ ፡ የማይስተው ፡ ሳኦል ፡ የተባለው
ዳዊት ፡ ላይ ፡ ወርውሮ ፡ ለምንድነው ፡ የሳተው
አዝኖለት ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ጋርዶት ፡ ነው (፪x)

የዚህ ፡ አለም ፡ ገዢ ፡ በጥልቅ ፡ ተቀምጦ
ሲፎክር ፡ አየሁት ፡ የእኔ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ
ሲፎክር ፡ ሰምቼ ፡ ልቤ ፡ ሲርድብኝ
ጌታ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እኔን ፡ ተናገረኝ

የፉከራ ፡ ድምፁን ፡ ሰምተህ ፡ ከምትፈራ
የተፃፈለትን ፡ ሂድ ፡ እና ፡ አንብበው
ቅዱሱን ፡ መጽሐፍ ፡ ገልጬ ፡ ሳነበው
የወንድሞች ፡ ከሳሽ ፡ ተጥሏል ፡ ነው ፡ እሚለው

እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x)

የጠላቴ ፡ ውጥኑ ፡ እቅዱ
ተስፋ ፡ ያረገው ፡ ክፉ ፡ ወጥመዱ
ባዶ ፡ ውሎ ፡ ባዶ ፡ አደረ
በአምላኬ ፡ እቅድ ፡ ተሰበረ

ያሰበው ፡ አልተሳካም ፡ ያሰበው (፬x)

ጳውሎስ ፡ ከባህር ፡ ላይ ፡ ከመርከብ ፡ አደጋ
ወደዳሩ ፡ ደርሶ ፡ እንደተረጋጋ
ብርድ ፡ ስለነበር ፡ እሳት ፡ እየሞቀ
ድንገት ፡ ከእጁ ፡ ላይ ፡ በእባብ ፡ ተነደፈ
ካሁን ፡ ካሁን ፡ አብጦ ፡ ይሞታል ፡ እያሉ
እዛው ፡ ይቀበራል ፡ ፡ ብለው ፡ ሲወያዩ
በእርጋታ ፡ መንፈስ ፡ እባቡን ፡ አራግፎ
ጌታን ፡ አገልግሏል ፡ ከእፉኝት ፡ ተርፎ

እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x)

ለብዙ ፡ ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ ጦር ፡ ከጁ ፡ ያልተለየው
ወርውሮ ፡ ወርውሮ ፡ የማይስተው ፡ ሳኦል ፡ የተባለው
ዳዊት ፡ ላይ ፡ ወርውሮ ፡ ለምንድነው ፡ የሳተው
አዝኖለት ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ጋርዶት ፡ ነው (፪x)

እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x)