በእኔ ፡ ዘመን (Benie Zemen) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

አንበጣ ፡ አይደለሁም ፡ ትንሽ ፡ ምናምንቴ
ፈቃድን ፡ አልሰጠውም ፡ እንዲስቅ ፡ ጠላቴ
በዘመኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ መልካሙን ፡ እናገራለሁ
የኢየሱስ ፡ ወንጌል ፡ በህይወቴ ፡ ላይ ፡ ሲሰራ ፡ አያለሁ

አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x)

አትደግ ፡ ብሎ ፡ ትላንት ፡ የረገመኝ
ጉድ ፡ ትሆናለህ ፡ ታያለህ ፡ እኮ ፡ ያለኝ
የርግማን ፡ ትንቢቱ ፡ ይፍረስ ፡ በጌታ ፡ ሥም
ልቤማ ፡ ደንግጦ ፡ ለርሱ ፡ እጅ ፡ አልሰጥም

አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x)

ከዘር ፡ ማንዘሮቼ ፡ ተወራርሶ ፡ የመጣ
ነፃነት ፡ ከልክሎ ፡ መንገዴን ፡ የዘጋ
ዛሬ ፡ በየሱስ ፡ ስም ፡ ጉልበቱ ፡ ይመታ
ወዳጄ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ በቤቴ ፡ ላይ ፡ ጌታ

አንበጣ ፡ አይደለሁም ፡ ትንሽ ፡ ምናምንቴ
ፈቃድን ፡ አልሰጠውም ፡ እንዲስቅ ፡ ጠላቴ
በዘመኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ መልካሙን ፡ እናገራለሁ
የኢየሱስ ፡ ወንጌል ፡ በህይወቴ ፡ ላይ ፡ ሲሰራ ፡ አያለሁ

አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x)

ውድቀቱን ፡ ለሚሹ ፡ ለሚመትቱበት ፡
በረከቱን ፡ ይዘው ፡ ሞት ፡ ለሚመኙለት ፡
ከሰማይ ፡ የሆነ ፡ ትንቢትን ፡ ይዣለሁ ፡
ለፃድቁ ፡ መልካም ፡ ይሆናል ፡ እላለሁ ፡

አንበጣ ፡ አይደለሁም ፡ ትንሽ ፡ ምናምንቴ
ፈቃድን ፡ አልሰጠውም ፡ እንዲስቅ ፡ ጠላቴ
በዘመኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ መልካሙን ፡ እናገራለሁ
የኢየሱስ ፡ ወንጌል ፡ በህይወቴ ፡ ላይ ፡ ሲሰራ ፡ አያለሁ

አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፪x)

ለቅዱሳን ፡ ሁሉ ፡ ክፉ ፡ የመደባችሁ
ሥም ፡ እየጠራችሁ ፡ እርገሙ ፡ ብሏቸው
የተናገሩት ፡ ቃል ፡ ይሁን ፡ ለራሳቸው
ያጠመዱት ፡ ወጥመድ ፡ ዞሮ ፡ ይያዛቸው

አዝ፦ በእኔ ፡ ዘመን ፡ መልካሙን ፡ መልካሙን ፡ አያለሁ (፬x)