ባሰብኝ (Basebegn) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

የአምላኩን ፡ ምሥጋና ፡ ካፉ ፡ እወስዳለሁ
በማመስገን ፡ ፈንታ ፡ ማጉረምረም ፡ እሞላለሁ
ያለው ፡ ከሳሼ ፡ ሳይሆንለት ፡ ቀርቶ
መላው ፡ ማንነቴ ፡ በደስታ ፡ ተሞልቶ

ባሰብኝ ፡ ምን ፡ ትሆን ፡ ጠላቴ
ባሰብኝ ፡ ይመስገን ፡ አምላኬ (፪x)

ሳላይ ፡ የሚያይልኝ ፡ ሳልሰማ ፡ ሚሰማ
ብጠራው ፡ ሚያደምጠኝ ፡ አምላክ ፡ አለኝና
አለቴ ፡ ውስጥ ፡ ሆኜ ፡ ወደ ፡ ውጭ ፡ እያየሁ
በሚፈልገኝ ፡ ላይ ፡ እስቅበታለሁ

አዝ፦ አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ
የማያልፈው ፡ ክፉ ፡ አጥቂ
አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ (፪x)

እልፍ ፡ ከሆኑት ፡ የጠላቴ ፡ እርግማኖች
መልካም ፡ ካልሆኑት ፡ አሰናካይ ፡ ንግግሮች
አንዲቱ ፡ ያምላኬ ፡ ምርቃት ፡ ከሱ ፡ እርግማን ፡ ትልቃለች
እስከ ፡ ሺህ ፡ ትውልድ ፡ በበረከት ፡ ታኖራለች

ይቀመጥ ፡ እንጂ ፡ ጠላቴ ፡ ሸንጎ
በመንገዴ ፡ ላይ ፡ ወጥመድ ፡ አድርጎ
ከራስ ፡ ፀጉሬ ፡ እስከ ፡ እግር ፡ ጥፍሬ
አለኝ ፡ ዋስትና ፡ አልሰጋም ፡ እኔ

አዝ፦ አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ
የማያልፈው ፡ ክፉ ፡ አጥቂ
አለኝ ፡ እና ፡ ጠባቂ (፪x)