አልነካም (Alnekam) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 3.jpg


(3)

ይቤዠኛል
(Yebezegnal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ወጣለሁ ፡ ገባለሁ ፡ በልዩ ፡ ጥበቃ
ኢየሱሴን ፡ አልፎ ፡ ማነው ፡ እኔን ፡ ሚነካ

አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም
በጠላቴ ፡ ላልነካ
ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x)

ከአቤል ፡ ደም ፡ ይልቅ ፡ የሚናገር ፡ ደሙ
እስከዛሬ ፡ ድረስ ፡ ትኩስ ፡ በመሆኑ
የወረወርው ፡ ቀስት ፡ ፈልጎ ፡ አጥቶኛል
የኢየሱሴ ፡ ደም ፡ በሙላት ፡ ጋርዶኛል

ኃይል ፡ አለውና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x)
ጋርዶኛልና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x)

ወጣለሁ ፡ ገባለሁ ፡ በልዩ ፡ ጥበቃ
ኢየሱሴን ፡ አልፎ ፡ ማነው ፡ እኔን ፡ ሚነካ

አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም
በጠላቴ ፡ ላልነካ
ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x)

ክፉ ፡ እንዲደሰት ፡ እንዲስቅ ፡ በእኔ
ደግሶ ፡ እንዲበላ ፡ አይፈቅድም ፡ መድህኔ
የቀባውን ፡ ሊያድን ፡ ይወጣል ፡ በግርማ
አድኖኝ ፡ ስላየሁ ፡ እላለሁኝ ፡ ዘና

ኃይል ፡ አለውና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x)
ጋርዶኛልና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x)

ወጣለሁ ፡ ገባለሁ ፡ በልዩ ፡ ጥበቃ
ኢየሱሴን ፡ አልፎ ፡ ማነው ፡ እኔን ፡ ሚነካ

አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም
በጠላቴ ፡ ላልነካ
ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x)

ምክር ፡ ተመክሮብኝ ፡ መልክተኞች ፡ መጡ
በክፉ ፡ ሴራቸው ፡ ህይወቴን ፡ ሊያጠምዱ
ሰፈሬ ፡ ሲደርሱ ፡ አልቻሉም ፡ ሊቀርቡኝ
በኢየሱሴ ፡ ደም ፡ ተሸፍኜ ፡ አዩኝ

ኃይል ፡ አለውና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x)
ጋርዶኛልና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x)

አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም
በጠላቴ ፡ ላልነካ
ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x)


eyasuse batayegn man nabar

Eyasus eyasuse dilene agahuegn Hulu barsu honaleg