ያን ፡ ዓመት ፡ እያስታወስኩኝ (Yan Amet Eyastaweskugn) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 4.jpg


(4)

ሕያው ፡ ምንጭ
(Heyaw Mench)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ያን ፡ ዓመት ፡ እያስታወስኩኝ
ያንን ፡ ወር ፡ እያስታወስኩኝ
ያንን ፡ ቀን ፡ እያስታወስኩኝ
ከአውሬው ፡ አፍ ፡ በአንተ ፡ እንደዳንኩኝ

አውቃለሁ ፡ ክብርን ፡ ምሥጋናን ፡ ለአንተ ፡ አመጣለሁ (፬x)

ስንት ፡ መስከረም ፡ ስንት ፡ ጥቅምት
ከእባብ ፡ ከጊንጡ ፡ የዳንኩበት
ስንት ፡ ህዳር ፡ ነበር ፡ ስንት ፡ ታህሳስ
ከሞት ፡ ያዳንከኝ ፡ ደርሰህ ፡ ኢየሱስ

ስንት ፡ ጥር ፡ አልፏል ፡ ስንት ፡ የካቲት
አለቀልኝ ፡ ብዬ ፡ ያልኩበት
ስንት ፡ መጋቢት ፡ ስንት ፡ ሚያዚያ
ሃዘን ፡ ሲሆነኝ ፡ መውጫና ፡ መግቢያ

ግንቦትስ ፡ ሰኔ ፡ ሐምሌ ፡ ነሃሴ
የጭንቅን ፡ ቀን ፡ አይቷል ፡ ይህ ፡ ነፍሴ
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ ደርሰህ ፡ ያዳንከኝ
እንዳመሰግን ፡ ዛሬን ፡ ሰጠኸኝ (፪x)

በጠዋት ፡ በቀትር ፡ ባመሻሽ ፡ በሌሊት
ስራህን ፡ ለማሰብ ፡ ብራመድ ፡ የኋሊት
ትዝ ፡ የሚሉኝ ፡ ማስታውሳቸው
የአንተን ፡ ማዳን ፡ ያየሁባቸው

እኮ ፡ እነዚያ ፡ የሄዱት ፡ አርቦች
ሃሙስ ፡ ቅዳሜ ፡ ብዙ ፡ እሁዶች
እሮቦቼ ፡ ማክሰኞ ፡ ሰኞ
ያልፍኳቸው ፡ ማዳንህ ፡ ገኖ

ይሁኑልኝ ፡ ለመታሰቢያ
የአንተን ፡ ማዳን ፡ ሁሌ ፡ ለማውሪያ
እንዲህ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ተመስገን
በአንተ ፡ ምህረት ፡ አለፈ ፡ ያ ፡ ቀን

አውቃለሁ ፡ ክብርን ፡ ምሥጋናን ፡ ለአንተ ፡ አመጣለሁ (፬x)

በሌሊት ፡ ከእንቅልፌ ፡ በድንገት ፡ ስነቃ
ቀኑን ፡ ላለማየት ፡ እል ፡ ነበር ፡ ባልነጋ
ባልነጋ ፡ ስላልኩኝ ፡ መች ፡ ቀርቶ ፡ ሳይነጋ
ቀኑን ፡ እንዳዘንኩኝ ፡ እደርስ ፡ ነበር ፡ ምሸትጋ

በጉስቁልናዬ ፡ አዘንክልኝና
ለነፍሴ ፡ ሰጠሃት ፡ የመጽናናት ፡ መና
ሌሊቶቼም ፡ ሆኑ ፡ መዝሙር ፡ መቀበያ
ቀኖቼም ፡ የአንተን ፈቃድ ፡ ማገልገያ

አውቃለሁ ፡ ክብርን ፡ ምሥጋናን ፡ ለአንተ ፡ አመጣለሁ (፬x)