ተመስገን (Temesgen) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 4.jpg


(4)

ሕያው ፡ ምንጭ
(Heyaw Mench)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 7:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ተመስገን ፡ የልቤ ፡ ፈውስ
የልቤ ፡ ጠጋኝ (፬x)

ክብር ፡ ይሁን ፡ የማጽናናትህ ፡ ደመና
ክብር ፡ ይሁን ፡ ዙራዬን ፡ ከቦታልና
ክብር ፡ ይሁን ፡ ሚያቋርጥ ፡ አይደል ፡ ደስታዬ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ምንጩ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ

የልቤ ፡ ጉልበት ፡ ይንበረከካል
ገብተህ ፡ ላከምከው ፡ ክብር ፡ ይሰጣል
ክብር ፡ ይሁንልህ (፪x)

ክብር ፡ ይሁንልህ (፬x)

እሩቅ ፡ ነው ፡ መንገዱ ፡ ይልቤ ፡ አድራሻ
ሰው ፡ አይደርስበትም ፡ ይቆማል ፡ ውጪው ፡ ጋር (፪x)

ልቤ ፡ ቢቆስልብኝ ፡ አካሚው ፡ አንተ ፡ ነህ
ከደጅ ፡ የማትቆም ፡ የምትገባ ፡ ዘልቀህ
ከደጅ ፡ የማትቆም ፡ የምትገባ ፡ ዘልቀህ
ክብር ፡ ይሁንልህ (፬x)

ማን ፡ አለኝ (፪x)
ከፊቴ ፡ እያለፈ ፡ የልቤን ፡ የሚረዳ
ዘልቆስ ፡ የሚጐበኝ ፡ የመንፈሴን ፡ ጓዳ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለልቤ ፡ መክፈቻ ፡ ያለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለውስጤ ፡ መክፈቻ ፡ ያለህ

ክብር ፡ ይሁን ፡ የማጽናናትህ ፡ ደመና
ክብር ፡ ይሁን ፡ ዙራዬን ፡ ከቦታልና
ክብር ፡ ይሁን ፡ ሚያቋርጥ ፡ አይደል ፡ ደስታዬ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ምንጩ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ

የልቤ ፡ ጉልበት ፡ ይንበረከካል
ገብተህ ፡ ላከምከው ፡ ክብር ፡ ይሰጣል
ክብር ፡ ይሁንልህ (፪x)

ክብር ፡ ይሁንልህ (፬x)