ላመልክህ ፡ የተገባህ (Lamelkeh Yetegebah) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 4.jpg


(4)

ሕያው ፡ ምንጭ
(Heyaw Mench)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ላመልክህ ፡ የተገባህ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ (፬x)

ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ

የማንንነቴ ፡ ምንጭ ፡ መገኛ ፡ ለሆንከው
    አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ
የሕይወት ፡ እስትንፋስ ፡ በውስጤ ፡ ላኖርከው
    አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ
ባአምሳልህ ፡ ፈጥረኸኝ ፡ አልሰግድም ፡ ለሌላ
    አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ
አምላክ ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ሚሆን ፡ የለምና
   አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ

ቢያጨበጭብ ፡ እጄ ፡ ዕልል ፡ ቢል ፡ ምላሴ
ስምህን ፡ ብትባርክ ፡ አምልጭ ፡ ያልካት ፡ ነፍሴ
ሁሉን ፡ ቻይነትህ ፡ ለእኔ ፡ ተገልጦ ፡ ነው
ምሥጋና ፡ አምልኮዬ ፡ ይገባሃል ፡ ምለው

መገኛዬ ፡ ነህ ፡ መገኛዬ
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ምሥጋናዬ
ፈጣሪዬ ፡ ነህ ፡ ፈጣሪዬ
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አምልኮዬ

ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ

ነፍሴን ፡ ከከበቧት የሆንክላት መዳን
    አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ
ውላ ፡ እንድታድር ፡ በሰላምህ ፡ ድንኳን
    አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ
የሕይወቴ ፡ ተስፋ ፡ እንዲያልፍ ፡ ከምድር
    አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ
ዓይኖቼን ፡ ያበራህ ፡ ለሰማዩ ፡ ሚስጥር
    አምልኮ ፡ የሚገባው ፡ ለአንተ

ቢያጨበጭብ ፡ እጄ ፡ ዕልል ፡ ቢል ፡ ምላሴ
ስምህን ፡ ብትባርክ ፡ አምልጭ ፡ ያልካት ፡ ነፍሴ
ሁሉን ፡ ቻይነትህ ፡ ለእኔ ፡ ተገልጦ ፡ ነው
ምሥጋና ፡ አምልኮዬ ፡ ይገባሃል ፡ ምለው

መገኛዬ ፡ ነህ ፡ መገኛዬ
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ምሥጋናዬ
ፈጣሪዬ ፡ ነህ ፡ ፈጣሪዬ
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አምልኮዬ

ላመልክህ ፡ የተገባህ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ (፬x)

ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ

ይሄው ፡ ይሄው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ነው
ይሄው ፡ ይሄው ፡ አምልኮዬ ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ነው (፪x)

ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ
ጌታ (፬x) ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ