From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሸቶናል ፡ የአንተ ፡ መገኘት ፡ ሸቶኛል
ሸቶኛል ፡ የአንተ ፡ ህልውና ፡ ሸቶኛል
እለመልማለሁ ፡ ብዙ ፡ አፈራለሁ
እለመልማለሁ ፡ ብዙ ፡ አፈራለሁ
አዝ፦ አልደርቅም ፡ አልደርቅም ፡ ሕያው ፡ ምንጭ
አንተ ፡ አለኸኝ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ዛፍ ፡ እንኳ ፡ ቢቆረጥ
ደግሞ ፡ ሊያቆጠቁጥ ፡ አዲስን ፡ ቅርንጫፍ
ሊያበቅል ፡ ተስፋ ፡ አለው
ለፍጥረት ፡ የመታደስን
ይህ ፡ እንደገና ፡ ተስፋን ፡ ሰጠኸው
ለእኔማ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ የነፍሴ ፡ ተስፋ
የምትበልጥ ፡ ለማቆጥቆጤ ከውኃ ፡ ሸታ
የክፉ ፡ ምሳር ፡ ቆርጦ ፡ :ሊጥለኝ
እስከወዲያኛው ፡ ከአንተ ፡ ሊለየኝ
ስመታ ፡ ተንገዳግጄ
ስደርስ ፡ ወደታች ፡ ስቧጥጥ
ሲብስ ፡ ማቃሰት ፡ ሆኖብኝ ፡ አንዳች
ሲሸተኝ ፡ የመገኘትህ ፡ የአንተ ፡ መዓዛ
ቆማለሁ ፡ ዳግም ፡ በጽኑ ፡ ምህረት ፡ ሲበዛ (፪x)
አዝ፦ አልደርቅም ፡ አልደርቅም ፡ ሕያው ፡ ምንጭ
አንተ ፡ አለኸኝ ፡ ኢየሱስ (፪x)
በድርቅ ፡ ዘመን ፡ ከቶ ፡ እንዳልሰጋ
ፍሬ ፡ ማፍራቴን ፡ ላይቆም ፡ አንዱ ፡ ጋር
እምነቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መታመኛዬ
ሙቀት ፡ ሲመጣ ፡ ላይፈራው ፡ ልቤ
ከአንተ ፡ አጠገብ ፡ ተተክያለሁ
ስለዚህ ፡ ሕይወቴ ፡ ሁሌ ፡ ለምለም ፡ ነው (፪x)
ሁሌ ፡ ለምለም ፡ ነው
ለመልማለሁ
|