አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ (Ategebie Honeh Tenafeqegnaleh) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 4.jpg


(4)

ሕያው ፡ ምንጭ
(Heyaw Mench)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 8:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

በቀንና ፡ በሌሊት ፡ አንተን ፡ እፈልጋለሁ
ልቤም ፡ አንተን ፡ አለ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ኢየሱስ ፡ እልሃለሁ
ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ
አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ
ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ
አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ

እፎይ ፡ ምልብህ ፡ ውስጤ ፡ ያለውን ፡ ሁሉ ፡ ተንፍሼ
በፊትህ ፡ ደስታ ፡ ሰላሜን ፡ ከልብስ ፡ ይልቅ ፡ ለብሼ
ልቤ ፡ ከናፍቆት ፡ አንተን ፡ ከማለት ፡ አይቆጠብም
ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆን ፡ ሚናፈቅ ፡ እንጂ ፡ አይጠገብም (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ
አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ
ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ
አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ

ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ኢየሱስ
ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ጣዕም ፡ ኢየሱስ (፪x)

ከገሃነም ፡ ጥርስ ፡ በአንተ ፡ መዳኔ ፡ በዝቶ ፡ ሳያንስ
በተከበበም ፡ መሃል ፡ ከተማ ፡ ሰላም ፡ ስትሆን
እረፍቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ቅጥሬ ፡ እንዳይናድ ፡ በዓለም ፡ ሁካታ
አብዝቼ ፡ እላለሁ ፡ አብረኸኝ ፡ ሆነህ ፡ ናፈቅከኝ ፡ ጌታ (፪x)

ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ኢየሱስ
ነህና ፡ ነህና ፡ የሕይወቴ ፡ ጣዕም ፡ ኢየሱስ (፪x)

መሄድ ፡ መሄድ ፡ መሄድ ፡ ወዳንተ ፡ መገኛ
ለነፍሴ ፡ ነውና ፡ ርሃቧ
ቀና ፡ አልልም ፡ ሌሊት ፡ አልልም ፡ አብዝቼ ፡ እፈልግሃለሁ
የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ የመኖሬ ፡ አላማ ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ያለው

ኦ ፡ አንተን ፡ ጌታ ፡ እፈልግሃለሁ (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ
አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ
ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለ
አጠገቤ ፡ ሆነህ ፡ ትናፍቀኛለህ (፪x)