አንተን ፡ ሳስብ (Anten Saseb) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 4.jpg


(4)

ሕያው ፡ ምንጭ
(Heyaw Mench)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

አንተን ፡ ሳስብ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ሳስብህ
አንተን ፡ ሳስብ ፡ ገና ፡ አንተን ፡ ሳስብህ
ወደ ፡ አምልኮ ፡ ባሕር ፡ ጠልቄ ፡ እሰጥማለሁ
ወደ ፡ አንተ ፡ መገኛ ፡ አድራሻ ፡ እየገባሁ
ስራዬ ፡ ስራዬ ፡ ማምለክ ፡ ነው
በቅኔ ፡ አንተን ፡ መባረክ ፡ ነው

ይሄው ፡ ጀመረኝ ፡ ለማመስገን ፡ በቅዱስ ፡ ስምህ ፡ መጉአደዱ
እንዲህ ፡ ይበሉ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አንተን ፡ ለማምለክ ፡ የወደዱ (፪x)

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ
ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር (፬x)

እንኳን ፡ እውነተኛ ፡ የሁሉም ፡ ባለቤት ፡ ሲከተል ፡ ልብ ፡ ያውቀው
ሰው ፡ ያመልክ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ እስትንፋስ ፡ ከሌለው ፡ አምላክ ፡ አበጅቶ
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ለእኛም ፡ በራልን ፡ ሚለው ፡ ቃል ፡ ከገባኝ
ለክብርህ ፡ ልዘምር ፡ ከጣኦታት ፡ መንደር ፡ ክንድህ ፡ ስላወጣኝ

አንተን ፡ ሳመልክህ ፡ ደስታ ፡ ቢያደርገኝ ፡ እንደሰከረ
ይሄ ፡ ጥቂት ፡ ነው ፡ ከዚህ ፡ ይብሳል ፡ እየጨመረ
ጌታ ፡ ሳመልክ ፡ ደስታ ፡ ቢያደርገኝ ፡ እንደሰከረ
ይሄ ፡ ጥቂት ፡ ነው ፡ ከዚህ ፡ ይብሳል ፡ እየጨመረ

ይሄው (፬x) ፡ የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፡ ኢሄው
ይሄው (፬x) ፡ የአንተን ፡ አምልኮ ፡ ጌታ ፡ ኢሄው
የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፡ ኢሄው
የአንተን ፡ አምልኮ ፡ ጌታ ፡ ኢሄው
የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፡ ኢሄው
የአንተን ፡ ዝማሬ ፡ ጌታ ፡ ኢሄው

አንተን ፡ ሳስብ ፡ ከጭንቀት ፡ ጐጆ ፡ ስር ፡ ወጥቼ ፡ በማመስገን ፡ ክንፍ ፡ እበራለሁ
አንተን ፡ ሳስብ ፡ ከፍ ፡ ያለብኝን ፡ በሙሉ ፡ ወደታች ፡ ማየት ፡ እጀምራለሁ
አንተን ፡ ሳስብ ፡ ማጉረምረም ፡ ግቢ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ውሎ ፡ ማደሪያ ፡ ሰፈሬ
አንተን ፡ ሳስብ ፡ ጌጠኛ ፡ ልብሴን ፡ ለብሼ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ሚልህ ፡ መዝሙሬ

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ
ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር (፬x)

ነፍሥም ፡ አይቀርልኝ ፡ የአንተን ፡ ማንነት ፡ ክብርህን ፡ አስቤ
ቅዱስ ፡ ሊል ፡ ይፈጥናል ፡ ታላቅነትህን ፡ ሊያመሰግን ፡ ልቤ
የምሥጋና ፡ ሽቶ ፡ ሳልቆጥብ ፡ ሳልሰስት ፡ ለክብርህ ፡ ላፍሰው
እንኳን ፡ ለደቂቃው ፡ ፳፬ ፡ ሰዓቱን ፡ ባመልክህ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው

የሰራኸኝ ፡ የፈጠርከኝ ፡ ለዚህ ፡ ነውና
ፈጽሞ ፡ አልጠግብም ፡ ዘምሬ ፡ አውርቼ ፡ የአንተን ፡ ምሥጋና (፪x)

አንተን ፡ ሳስብ ፡ ከጭንቀት ፡ ጐጆ ፡ ስር ፡ ወጥቼ ፡ በማመስገን ፡ ክንፍ ፡ እበራለሁ
አንተን ፡ ሳስብ ፡ ከፍ ፡ ያለብኝን ፡ በሙሉ ፡ ወደታች ፡ ማየት ፡ እጀምራለሁ
አንተን ፡ ሳስብ ፡ ማጉረምረም ፡ ግቢ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ውሎ ፡ ማደሪያ ፡ ሰፈሬ
አንተን ፡ ሳስብ ፡ ጌጠኛ ፡ ልብሴን ፡ ለብሼ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ሚልህ ፡ መዝሙሬ

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ
ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር (፬x)