እንዲሁ በነፃ (Track 7) - ኤሎራ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤሎራ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን
(Elora Gospel Singers)

Lyrics.jpg


(1)

ዘጸአት
(Exodus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2019)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 05:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤሎራ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Elora Gospel Singers)

ያደረኩት የለም ስለ መዳኔ ፪
የከፋልኩት የለም ስለ መዳኔ ፪
እንዲሁ በነፃ የዳንኩት ፬
እንዲሁ በፀጋ ነው ፬

ጌታ ኢየሱስ ነው ለኔ የሞተልኝ
ከሐጥያት እርግማን ነፃ ያወጣኝ
ራሱን ስለ እኔ በርግጥ ሰውቶታል
ነፍሴን ሊያድናት ደም ከፍሎላታል

ወዶኝ ስላዳነኝ የለብኝ ኩነኔ
እዳዬ ተከፍሎልኛል ነፃ ነኝ እኔ
ስራዬን መስቀል ላይ ሰርቶ ጨርሶታል
በሞቱ ህይወቴን ከሞት ዋጅቷታል

ያደረኩት የለም ስለ መዳኔ ፪
የከፋልኩት የለም ስለ መዳኔ ፪
እንዲሁ በነፃ የዳንኩት ፬
እንዲሁ በፀጋ ነው ፬

ግራ አልተጋባሁም አልተቅበዘበዝኩም
ድነትን ፍለጋ እየዞርኩ ወጥቼ አልወረድኩም
በማመኔ ብቻ በልጁ በኢየሱስ
እኔን አድርጐኛል በአብ ቀኝ
ከርሱ ጋር እንድወርስ

ቤቴን በሰማይ እርሱ ሰርቶልኛል
መኖርያዬን በላይ አዘጋጅቶልኛል
አርፌያለው በርሱ በነፍስ በስጋዬ
የዘላለም ህይወት ሰጥቶኝ እያሱስ ጌታዬ

እንድሁ በነፃ ፬
እንድሁ በፀጋ ፬
እንድሁ በነፃ ፬
እንድሁ በፀጋ ፬