ኢየሱስ ያድናል (Track 4) - ኤሎራ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤሎራ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን
(Elora Gospel Singers)

Lyrics.jpg


(1)

ዘጸአት
(Exodus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2019)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 05:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤሎራ ፡ የወንጌል ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Elora Gospel Singers)

ከላይ ወርዶ ለኛ ስለሞተው
የተነሳው ደግሞም የሚመጣው
የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ
እርሱ ብቻ ነው ከሞት የሚያድነው።
በእርሱም አምነን ከጥፋት ድነናል
የዘላለም ህይወት አግኝተናል ።
ከሚያምኑት ከቅዱሳን ጋራ
የመንግስቱ ወራሾች ሆነናል ።

በልጁ በኢየሱስ ያመነ ህይወት አለው
ማንም በእርሱ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፡ ፬x

ያለ ጌታ ኢየሱስ አማላጅነት
ዓለም ሁሉ ሊደን በጭራሽ አይችልም ።
እውነት መንገድ ህይወት እርሱ ነውና
ወደ አብ መድረሻ ሌላ የለም ።
መዳን ከእርሱ በቀር በማንም የለም
ለአለም ሁሉ የሞተው ኢየሱስ ብቻ ነው ።
እንድንበት ዘንድ ለኛ የተሰጠን
የናዝሬቱ የእየሱስ ስም ነው ።
    
    እየሱስ ያድናል
    ከሲኦል ገሃነም እሳት
    እየሱስ ያድናል
    ከጨለማው ዘላለም ሞት
    እየሱስ ያድናል
    ያድናል ይታደጋል
    እየሱስ ያድናል
    ህይወትን ይሰጣል

ከላይ ወርዶ ለኛ ስለሞተው
የተነሳው ደግሞም የሚመጣው
የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ
እርሱ ብቻ ነው ከሞት የሚያድነው።
በእርሱም አምነን ከጥፋት ድነናል
የዘላለም ህይወት አግኝተናል ።
ከሚያምኑት ከቅዱሳን ጋራ
የመንግስቱ ወራሾች ሆነናል ።

በልጁ በኢየሱስ ያመነ ህይወት አለው
ማንም በእርሱ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፡ ፬x

ማንስ ለማን በእርሱ ፈንታ እሞታለሁ
ብሎ የራሱን ነፍስ አሳልፎ ይሰጣል?
ያለ ሀጥያቱ የሌላውን ሀጥያት
ለራሱ ወስዶ ማን ይሸከማል?
እየሱስ ግን ራርቶ ይህን አደረገ
እኛ ነፃ አወጣን ለሁላችን ሞቶ
ከሰማያት ወርዶ ዝቅ ዝቅ አለ
አምላክነቱን ክብሩንም ትቶ ።

    እየሱስ ያድናል
    ከሲኦል ገሃነም እሳት
    እየሱስ ያድናል
    ከጨለማው ዘላለም ሞት
    እየሱስ ያድናል
    ያድናል ይታደጋል
    እየሱስ ያድናል
    ህይወትን ይሰጣል