የነፍሴ ፡ ንጉሥ (Yenefsie Negus) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Lyrics.jpg


(Volume)

ስብስብ
(Collection 2)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 3:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x)

በድንግዝግዝ ፡ ብርሃን ፡ በምኞት ፡ ሸለቆ
ቆሜ ፡ ሳነባ ፡ አየኝ ፡ ሕይወቴ ፡ ተነክቶ
የዘረጋው ፡ እጁ ፡ አልደርስለት ፡ ብሎ
አወጣኝ ፡ አምላኬ ፡ ለእኔ ፡ ተንጠልጥሎ

አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x)

እጆቹ ፡ ቆሰሉ ፡ ግንባሩ ፡ ተበሳ
ለእኔ ፡ ለሙት ፡ ሕይወት ፡ እንዲኖረኝ ፡ ተስፋ
ጐኑን ፡ ለጦር ፡ ሰጥቶ ፡ ደሙን ፡ አጐረፈ
የእኔን ፡ አፈር ፡ ገላ ፡ ከሞት ፡ አተረፈ

አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x)

ጀርባውን ፡ ለጅራፍ ፡ አጋልጦ ፡ ሰጠና
ተዘነጋ ፡ በእርሱ ፡ የእኔ ፡ ጉስቁልና
እርቃኑን ፡ ተጋልጦ ፡ ሆኖ ፡ ጐስቋላ ፡ ሰው
ሚስጢሬን ፡ ደብቋል ፡ ሕይወቴ ፡ እንዴት ፡ ትርሳው?

አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x)

የድካሙ ፡ ብዛት ፡ ለእኔ ፡ ፋታ ፡ ሆነኝ
የቀራንዮ ፡ ደም ፡ ከኃጢአት ፡ አዳነኝ
ጽድቁን ፡ ተመርኩዤ ፡ ስራዬን ፡ ደብቄ
ተጓዝኩኝ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ድካሜን ፡ አውቄ

አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x)