እፈልግሀለሁ (Lord I need you) - ዳዊት ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Lyrics.jpg


(Volume)

ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(singles)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

አንተ ፡ የልቤ ፡ ረሃብ ፡ የነፍሴ ፡ ጥማት
ልቤን ፡ የወሰድከው ፡ አንተ ፡ ካለህበት
ከምትገኝበት
በመቅደስህ ፡ ሆነህ ፡ ሁሌ ፡ አስብሀለሁ
ደስ ፡ የሚያሰኘውን ፡ ፊትህን ፡ እሻለሁ
እፈልግሀለሁ


እንደምትናፍቅ ፡ ዋላ ፡ ወደ ፡ ውሀ
አግኝታህ ፡ እስክትረካም ፡ ከዛ ፡ በበረሀ
ምንም ፡ አይታያት ፡ ማንም ፡ አያስቆማት
እንዲሁ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ የነፍሴ ፡ ጥማት ፪x

አገኘሁ ፡ እና ፡ ጥሜን ፡ አረካኸው
ግን ፡ ደግሞ ፡ እርካታዬ ፡ አንተን ፡ ሚያስናፍቅ ፡ ነው
አሁንም ፡አሁንም ፡ ልቤ ፡ ይፈልግሀል
በነገሮች ፡ መሀል ፡ ሀሳቤ ፡ ይወሰዳል
ወደ ፡ አንተ ፡ ይሄዳል


አንተ ፡ የልቤ ፡ ረሃብ ፡ የነፍሴ ፡ ጥማት
ልቤን ፡ የወሰድከው ፡ አንተ ፡ ካለህበት
ከምትገኝበት
ዋና ፡ የልቤ ፡ ትኩረት ፡ የዓይኔ ፡ ደግሞ ፡ ፍዘት
የጆሮዬ ፡ ጉጉት ፡ ድምፅህን ፡ ለመስማት
በእጅህ ፡ ለመነካት


ረሃቤ ፡ ክብርህ ፡ ነው ፡ ውበትህ ፡ ጥማቴ
በሰማዩ ፡ ስርዐት ፡ ተወስዷል ፡ መሻቴ
የምድርን ፡ ግሳንግስ ፡ ትቼ ፡ ወደ ፡ ኋላ
ወደ ፡ አንተ ፡ እሮጣለሁ ፡ ዘወትር ፡ እንድሞላ
ረሃቤ ፡ ነህና


አንተ ፡ የልቤ ፡ ረሃብ ፡ የነፍሴ ፡ ጥማት
ልቤን ፡ የወሰድከው ፡ አንተ ፡ ካለህበት
ከምትገኝበት
ዋና ፡ የልቤ ፡ ትኩረት ፡ የዓይኔ ፡ ደግሞ ፡ ፍዘት
የጆሮዬ ፡ ጉጉት ፡ ድምፅህን ፡ ለመስማት
በእጅህ ፡ ለመነካት

በየዕለቱ ፡ ሙላኝ ፡ ልቤንም ፡ ለውጠው
በኢየሱስ ፡ የነበረውን ፡ ሀሳብ ፡ በእኔም ፡ ደግሞ ፡ ሙላ
በትላንቱ ፡ ሙላት ፡ ትዝታ ፡ መኖር ፡ አልፈልግም
ዛሬም ፡ ትሻሀለች ፡ ነፍሴ ፡ እንደ ፡ አዲስ
ከቶ ፡ አልለምድህም


እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ እሻሀለሁ
እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ፡ ኃይሌ ፡ አንተን ፡ እሻሀለሁ
እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ እሻሀለሁ
እፈልግሀለሁ ፪x
በሙሉ ፡ ኃይሌ ፡ አንተን ፡ እሻሀለሁ