እፈልግሃለው (Efelighihalew) - ዳዊት ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(Esp)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

አንተ የልቤ ረሃብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት - ከምትገኝበት
በመቅደስህ ሆነህ ሁሌ አስብሃለሁ
ደስ የሚያሰኘውን ፊትህን አሻለሁ - አፈልግሃለሁ

አንደምትናፍቅ ዋላ ወደ ውሃ
አግኝታ እስክትረካ በዚያ በበረሃ
ምንም ባይታያት ማንም አያስቆማት
እንዲሁ አምላኬ ነው የነፍሴ ጥማት (2)
አገኘሁህ እና ጥሜን አረካሀው
ግን ደግሞ ርካታዬ አንተን ሚያስናፍቅ ነው
አሁንም አሁንም ልቤ ይፈልግሃል
በነገሮች መሃል ሃሳቤ ይወሰዳል - ወዳንት ይሄዳል

አንተ የልቤ ረሃብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት - ከምትገኝበት
ዋናው የልቤ ትኩረት - የአይኔ ደግሞ ፍዘት
የጆሮዬ ጉጉት ድምጽህን ለመስማት - በእጅህ ለመነካት

ረሃቤ ክብርህ ነው ውበትህ ጥማቴ
በሰማዩ ስርዓት ተወስዷል መሻቴ
የምድርን ግሳንግስ ትቼ ወደህዋላ
ወዳንተ እሮጣለሁ ዘወትር እንድሞላ - ?????

አንተ የልቤ ረሃብ የነፍሴ ጥማት
ልቤን የወሰድከው አንተ ካለህበት - ከምትገኝበት
ዋናው የልቤ ትኩረት - የአይኔ ደግሞ ፍዘት
የጆሮዬ ጉጉት ድምጽህን ለመስማት - በእጅህ ለመነካት

በየለቱ ሙላኝ ልቤንም ለውጠው
በኢየሱስ የነበረውንሃሳብ - በኔም ደግሞ ሙላው
በትላንቱ ሙላት ትዝታ መኖር አልፈልግም
ዛሬም ትሻሃለች ነፍሴ እንዳዲስ - ከቶ አልለምድህም

እፈልግሀለሁ እፈልግሀለሁ
በሙሉ ልቤ አንተን እሻሃለሁ
እፈልግሀለሁ እፈልግሀለሁ
በሙሉ ኃይሌ አንተን እሻሃለሁ