ዘለዓለም አይጠፋም (Zelalem Aytefam) - ዳዊት ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Dawit Getachew 1.jpg


(1)

እጠብቅሃለሁ
(Etebeqehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

ሥራህን ፡ ለመግለፅ ፡ አንደበት ፡ ቢያንሰኝም
ከምሥጋና ፡ በቀር ፡ የምለው ፡ የለኝም
ሳወራው ፡ እኖራለሁ ፡ እስከ ፡ ለዘለዓለም
ያደረከው ፡ ሁሉ ፡ ከልቤ ፡ አይጠፋም

ጊዜው ፡ ቢርቅ ፡ ብዙ ፡ ቢያልፍም
ከልቤ ፡ ውስጥ ፡ ከቶ ፡ አይጠፋም
ከዚህ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም

አዝ:- ዘለዓለም ፡ አይጠፋም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅርህ
ያደረከው ፡ ሁሉ ፡ ዉለታህ
ከቶ ፡ አልረሳውም ፡ ታትሟል ፡ በልቤ
የዘለዓለም ፡ ፍቅሬ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ

መገረፍ ፡ መድማትህ ፡ ለእኔ ፡ መሞትህ
ከጥፋት ፡ እንዳመልጥ ፡ ከክብርህ ፡ መውረድህ
ከተወጋው ፡ ጐንህ ፡ የፈሰሰው ፡ ደምህ
ዘወትር ፡ ትዝ ፡ ይለእኛል ፡ ኢየሱስ ፡ መከራህ

የመስቀሉ ፡ ዉለታህ ፡ ለእኔ ፡ ትልቅ ፡ ትዝታ ፡ ነው ፡ መድህኔ
ሕይወትን ፡ ሰጥተህ ፡ አድነኀኛል
ፍቅርህ ፡ ከልቤ ፡ ወስጥ ፡ እንዴት ፡ ይጠፋል

አዝ:- ዘለዓለም ፡ አይጠፋም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅርህ
ያደረከው ፡ ሁሉ ፡ ዉለታህ
ከቶ ፡ አልረሳውም ፡ ታትሟል ፡ በልቤ
የዘለዓለም ፡ ፍቅሬ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፪x)

ዓይኔ ፡ ሌላ ፡ ከቶ ፡ አያይም
ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ውስጥ ፡ ሰርጾ ፡ ገብቷል
ማንም ፡ ሳይቀይረው ፡ ይኖራል