From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ኃያላን ፡ ሲነሱ ፡ እርስ ፡ በዕርሳቸው
ምድር ፡ ስትናወጥ ፡ ግራ ፡ ሲገባቸው
ቀኑ ፡ ሲደርስ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ስትመጣ
ያን ፡ ጊዜ ፡ ያበቃል ፡ የዚች ፡ ዓለም ፡ ጣጣ
አዝ:- ናፍቃለሁ ፡ ያንን ፡ ቀን ፡ ላይ ፡ ሁልጊዜ ፡ እሮጣለሁ
የተሰቀለውን ፡ የሞተውን ፡ የተነሳውን ፡ ላየው
የመላዕክት ፡ ድምፅ ፡ ዝማሬያቸው ፡ ከሩቁ ፡ ይሰማኛል
የምጠብቀው ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መምጫው ፡ ጊዜ ፡ ደርሷል
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ ምንም ፡ አይጐድለንም
በሰማይ ፡ ቤት ፡ ስቃይ ፡ ጉስቁልና ፡ የለም
እንዘምራለን ፡ ዘለዓለም ፡ በደስታ
ለይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ
አዝ:- ናፍቃለሁ ፡ ያንን ፡ ቀን ፡ ላይ ፡ ሁልጊዜ ፡ እሮጣለሁ
የተሰቀለውን ፡ የሞተውን ፡ የተነሳውን ፡ ላየው
የመላዕክት ፡ ድምፅ ፡ ዝማሬያቸው ፡ ከሩቁ ፡ ይሰማኛል
የምጠብቀው ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መምጫው ፡ ጊዜ ፡ ደርሷል
ጌታ ፡ ሲመጣ ፡ በመላእክት ፡ ታጅበን
ከሙሽራው ፡ ጋር ፡ ልንኖር ፡ አብረን ፡ እንሄዳለህ
የሚያሰጋን ፡ የለም ፡ ዕዳችን ፡ ሁሉ ፡ ተከፍሏል
በነጽነት ፡ ልንኖር ፡ ከእርሱ ፡ ጋር
ዳግመኛ ፡ በክብር ፡ ይመጣል (፪x)
ጌታ ፡ ሲመጣ ፡ በመላእክት ፡ ታጅበን
|