ሁኔታዎችን (Hunietawochin) - ዳዊት ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Dawit Getachew 1.jpg


(1)

እጠብቅሃለሁ
(Etebeqehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

ሁኔታዎችን ፡ አይቼ ፡ ተመስገን ፡ አልልህም
ያሰብኩት ፡ ባይሳካ ፡ አፌን ፡ አላበላሽም
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ በእውነት ፡ ጻድቅ ፡ ነህ
የሚሳንህ ፡ አንዳች ፡ የለም
ይሆናል ፡ አይሆን ፡ ብዬ ፡ በዚህ ፡ አልገመግምህም

ለባህር ፡ ገደብን ፡ ሰጠህ
ከዚህ ፡ አትለፍ ፡ ብለህ
ፀሀይም ፡ በማለዳ ፡ በቃልህ ፡ ያጸና
አንተ ፡ ስትናገር ፡ የማይሆን ፡ የቱ ፡ ነው
ሁኔታን ፡ አይቼ ፡ ክፉ ፡ አይወጣኝም ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ለበጎ ፡ ነው

አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም
በሞት ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ብራመድ ፡ ክፉውን ፡ እኔ ፡ አልፈራም
ብታድነኝ ፡ ባታድነኝም ፡ ብትሰጠኝ ፡ ብትነሳኝም
አምልኮ ፡ ስራዬ ፡ እንጂ ፡ የሕይወቴ ፡ ጊዜያዊው ፡ ስሜት ፡ አይደለም

ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ ፡ በስራህ ፡ አትሳሳትም
አማካሪ ፡ አትፈልግ ፡ የትኛው ፡ ነገር ፡ አቅቶህ
ስለዚህ ፡ ራሴን ፡ እንቃለው ፡ በምትሰራው ፡ ስራ
ምህረትህ ፡ ለእኔ ፡ ይብዛልኝ
ለሃጥያቴ ፡ ከማውቅህ ፡ በላይ ፡ ነህና