ጌታ ፡ ሆይ (Gieta Hoy) - ዳዊት ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Dawit Getachew 1.jpg


(1)

እጠብቅሃለሁ
(Etebeqehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 3:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

ሽክሜን ፡ እና ጭንቀቴን
በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ
ያለፈው ፡ ይበቃኛል
መለወጥን ፡ እሻለሁ

አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ የልመናዬን ፡ ቃል ፡ ስማ
ፀሎቴንም ፡ መልስልኝ ፡ እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ታደገኝ
በእራሴ ፡ ብዙ ፡ ደክሜያለሁ ፡ ስለፋ
የማላውቀውን ፡ ተስፋ ፡ ዕድሜዬን ፡ ሙሉ ፡ ስለፋ

የአንተን ፡ የልብህን ፡ ሃሳብ ፡ እየፈጸምኩኝ ፡ መኖር ፡ እሻለሁ
ከዚህች ፡ ዓለም ፡ ከንቱ ፡ ነገር ፡ ዐይኔንም ፡ አነሳዋለሁ
ዋጋ ፡ አለውና ፡ የከበረ ፡ እርሱን ፡ ለመያዝ ፡ እዘረጋለሁ
ከእንግዲህ ፡ በቀረኝ ፡ እድሜ ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ እሻለሁ

ባለማስተዋል ፡ የሰበሰብኩት
ከንቱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ለካስ ፡ ያከማቸሁት
ክፋቴን ፡ ሁሉ ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ሳየው
እራሴን ፡ ስወቅስ ፡ ደግሞ ፡ እገኛለሁ
ደግሞ ፡ እንደገና ፡ ነግቶልኝ ፡ ስሮጥ
አንድ ፡ ዐይነት ፡ ሕይወት ፡ የማይለወጥ
ይህ ፡ ከንቱ ፡ ኑሮ ፡ ብዙ ፡ ደከመኝ
አሁን ፡ ግን ፡ በቃኝ ፡ ባክህ ፡ ለውጠኝ

አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ የልመናዬን ፡ ቃል ፡ ስማ
ፀሎቴንም ፡ መልስልኝ ፡ እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ታደገኝ
በእራሴ ፡ ብዙ ፡ ደክሜያለሁ ፡ ስለፋ
የማላውቀውን ፡ በተስፋ ፡ ዕድሜዬን ፡ ሙሉ ፡ ስለፋ