በማዕበል ውስጥ ሆኖ (Bemaebel wust hono) - ዳዊት ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Dawit Getachew 1.jpg


(1)

እጠብቅሃለሁ
(Etebeqehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

በማዕበል ፡ ውስጥ ፡ ሆኖ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መሄድ ፡ ነው (፪x)
በወጀብም ፡ መሃል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መሄድ ፡ ነው ፡ መሄድ ፡ ነው
በባሕር ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ በሚያስፈራራው
ተሽመድምዶ ፡ መቅረት ፡ ለምንድን ፡ ነው ፡ ግራ ፡ እንደገባው
ከቶ ፡ ለምን ፡ ይሆን ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ የምንፈራው
የዘወትር ፡ ልመና ፡ አሃሃሃ ፡ የምናደርሰው

አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ዓይኖቻችንን ፡ ክፈተው
በእውነት ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ መሆንህን ፡ እንድናውቀው (፪x)
አንተ ፡ እያለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ከጐናችን
እንፈራለን ፡ ወጀብን ፡ እያየን
እምነታችንም ፡ በሁኔታዎች ፡ ጥለን
ወየሁ ፡ ጠፋን ፡ እያልን ፡ እንጮሃለን
ከእንግዲህ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ቀና ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን
ወጀቡን ፡ እንፈራውም ፡ በስምህ ፡ እንረግጠዋለን

ለአእዋፍ ፡ ሁሉ ፡ የምታጠግብ ፡ ነህ
ለእኛ ፡ ለልጆችህ ፡ እንዴት ፡ ትነሳለህ
ብታደርግ ፡ ሁልጊዜ ፡ አሃ ፡ መች ፡ እናውቅሃለን
ስለሚቀጥለው ፡ ደግሞ ፡ ብዙ ፡ እናስባለን
ጌታ ፡ አንተን ፡ ብናይ ፡ አሃ ፡ ይህ ፡ ባልሆነ ፡ በእኛ
እምነት ፡ ጨምርልን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምነው ፡ በ. (1) .


አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ዓይኖቻችንን ፡ ክፈተው
በእውነት ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ መሆንህን ፡ እንድናውቀው (፪x)
አንተ ፡ እያለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ከጐናችን
እንፈራለን ፡ ወጀብን ፡ እያየን
እምነታችንም ፡ በሁኔታዎች ፡ ጥለን
ወየሁ ፡ ጠፋን ፡ እያልን ፡ እንጮሃለን
ከእንግዲህ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ቀና ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን
ወጀቡን ፡ እንፈራውም ፡ በስምህ ፡ እንረግጠዋለን

አንፈራም ፡ ወጀቡን ፡ አንፈራም ፡ አንፈራም