አትተወኝ (Atetewegn) - ዳዊት ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Dawit Getachew 1.jpg


(1)

1
(1)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:46
ጸሐፊ (Writer): ዳግማዊ ሞገስ
(Dagimawi Moges
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

ምክንያት : አላቀርብም : ለኃጢአቴ
ራሴን : አውቀዋለሁ : ማንነቴን
አንተ : ግን : ጻጽቅ : ነህ : ለዘለዓለም
ታውቀኛለህና : የትም : አልሄድም

አሳዝኜሃለሁ : እውነት : ነው
አላስከበርኩህም : አውቃለሁ
ነገር : ግን : ጌታ : ሆይ : ማረኝ : እላለሁ
ምህረትህ : ብዙ : ነው : አንጻኝ : ነጻለሁ

ከፊትህ : አትጣለኝ : ከቶ : ዝም : አትበለኝ
ቅዱሱን : መንፈስህን : ከ : እኔ : አትውሰድብኝ
መለወጥ : እሻለሁ : ከ : ኃጢአቴ : አንጻኝ
በደምህ : እጠበኝ : እኔም : እነጻለሁኝ

ኃጢአተኝነቴ : እጅግ : አሳዝኖህ
ትተኸኝ : እንዳትሄድ : ለፈቃዴ : ሰጥተህ
እኔ : ባሳዝንህም : አትተወኝ : እባክህ
መሃሪ : ነህና : በ : እጅህ : ላይ : ጣለኝ

አሳዝኜሃለሁ : እውነት : ነው
አላስከበርኩህም : አውቃለሁ
ነገር : ግን : ጌታ : ሆይ : ማረኝ : እላለሁ
ምህረትህ : ብዙ : ነው : አንጻኝ : ነጻለሁ

ኃጢአተኛን : ትተህ : ጨክነህ : ብትሄድ
ማን : ይመልሰዋል : ከሲዖል : መንገድ
እኔም : ወደ : ሲዖል : ብሄድ : ማን : ያድነኛል
በእጅህ : ላይ : መጣል : እርሱ : ይሻለኛል