ይመጣል (Yimetal) - ዳዊት ጌታቸው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Lyrics.jpg


(2)

አምንሀለው
(Amnhalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:19
ጸሐፊ (Writer):
(Dawit Getachew
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

እንዴት እንሆን ይሆን ፡ ፊትለፊት ስናየው
ያዘጋጀነውን ፡ ጥያቄ ፡ ትተነው
ፈዘን በውበቱ ፡ በሚያስደንቅ ግርማው
አይን አይኑን እያየን ፡ እሱን ማወደስ ነው

ይመጣል በግርማው ፡ ይመጣል በክብር
ሊወስደን እንድንኖር ፡ ከእርሱ ጋር
ተስፋችን ኢየሱስ ፡ በሀይል ይገለጣል
የወጉትም ደግሞ ፡ በአይናቸው ያዩታል
የእርሱ የሆኑትን ግን ፡ ሊወስድ ይመጣል

ማደሪያው ከእኛ ጋር ነው ፡ እግዚአብሔር እራሱ
ህመም ወይም ሀዘን ፡ በዛ አይሠማም
እንባችንን በሙሉ ፡ ታብሶ ከአይናችን
ከኢየሱስ ጋር ልንኖር አብረን እንሄዳለን

ይመጣል በግርማው ፡ ይመጣል በክብር
ሊወስደን እንድንኖር ፡ ከእርሱ ጋር
ተስፋችን ኢየሱስ ፡ በሀይል ይገለጣል
የወጉትም ደግሞ ፡ በአይናቸው ያዩታል
የእርሱ የሆኑትን ግን ፡ ሊወስድ ይመጣል

አዲሷ ኢየሩሳሌም ፡ ውበቷ የከተማው
የእግዚአብሔር ክብር እና ፡ በጉ ብርሀኗ ነው
ፀሀይ ወይም ጨረቃ ፡ ከቶ አያስፈልግም
የአምላኬ መገኘት ፡ ያበራዋል ሁሉንም

እንሄዳለን በክብር ፡ ልንኖር ከእርሱ ጋር
ይመጣል በክብር ፡ ልንኖር ከእርሱ ጋር