From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ዳዊት ጌታቸው (Dawit Getachew)
|
|
፪ (2)
|
አምንሃለሁ (Aminhalehu)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ ፬ (2021)
|
ቁጥር (Track):
|
፫ (3)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:10
|
ጸሐፊ (Writer):
|
ዳዊት ጌታቸው (Dawit GetachewProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የዳዊት ጌታቸው ፡ አልበሞች (Albums by Dawit Getachew)
|
|
ሰዉን : ሁሉ : የሚያድን : የእግዚአብሄር : ፀጋ : በክርስቶስ : በኩል : ተገልጧል
ለሚያምን : ሁሉ : የኃጢያት : ስርየት : እንዲሁ : በነፃ : ያደርጋል
ተስፋ : ለቆረጡ : ለተጨነቁ : በሞት : ጥላ : ውስጥ : ላሉ :ሁሉ
ወደ : ህይወት : መንገድ : ይመራቸዋል : ጉልበት : አለው : ደሙ
አዝ:- ፀጋው : በእምነት : አድኖናል
ክርስቶስ : ቤዛ : ሆኖልናል
ይህም : የእግዚአብሄር : ስጦታ : እንጂ
ከእኛ : ስላይደለ : ከቶ : እንደለፋንበት : አንመካም
ቅን : ፈራጅ : ጻድቅ : አምላክ : ነው : እና : እንከን : የሌለበት
ኃጢያተኛውን : ሊያጸድቅ : ወዶ : ልጁን : አደረገው : ኃጢያት
እዉነትን : እና : ምህረትን : አስማምቶ : እኛን :አፀደቀን
በክርስቶስ : በኩል : በነፃ : የተሰጠን : የፀጋው : ክብር : ይመስገን
አዝ:- ፀጋው : በእምነት : አድኖናል
ክርስቶስ : ቤዛ : ሆኖልናል
ይህም : የእግዚአብሄር : ስጦታ : እንጂ
ከእኛ : ስላይደለ : ከቶ : እንደለፋንበት : አንመካም
ስለሚገባን : ሳይሆን : እንዲው : ስለወደደን
ከዘላለም : ሞት : ሊያድነን : ፀጋውን : ላከልን
እያስተማረ : እየረዳ : እስከፍጻሜው : ሊያደርሰን
እግዚአብሄርን : እንድንመስል : ፀጋው : ነው : የሚረዳን
በፀጋው : ክብር : ይሁን
ላዳነን : ክብር : ይሁን
ለኢየሱስ : ክብር : ይሁን
ይገባዋል : እና : ክብር : እና : ምስጋና : አሜን
በፀጋው : ክብር : ይሁን
ላዳነን : ክብር : ይሁን
ለኢየሱስ : ክብር : ይሁን
አድኖናል : እና : እንዲሁ : በፀጋ : አሜን
|