ኦ ነፍሴ (Oh Nefse) - ዳዊት ጌታቸው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Lyrics.jpg


(2)

አምንሀለው
(Amnihalehu)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:34
ጸሐፊ (Writer): ዳዊት ጌታቸው
(Dawit Getachew
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

ነፍሴ : ሆይ : አስቢ : ያደረገልሽን : እግዚአብሔር
ከጥፋት : ከልሎ : እዚህ : ያደረሰሽን : ሆኖሽ : ቅጥር
ከደዌሽ : በሙሉ : የፈወሰሽ
በጭንቅ : ሰዓት : የደረሰልሽ

ጎልማሳነትሽን : እንደ : ነስር : ጉልበት : የሚያድሰው
ምኞትሽን : ከበጎ : ነገር : የሚያረካ : እግዚአብሔር : ነው
ህይወትሽን : ያዳነ : ከጥፋት : መንገድ
ከፊት : ለፊትሽ : ቀድሞ : የሚሄድ

የውስጥ : ሰውነቴ : ቅዱስ : ሰሙን
በቀንም : በማታ : አክብሩት : እርሱን
እግዚአብሔር : መሃሪ : ይቅር : ባይ : ነውና
ነፍሴ : ሆይ : እያሰብሽ : አቅርቢ : ምስጋና

   አዝ፦ ኦ : ነፍሴ : እባክሽ
      ምህረቱን : እያሰብሽ : አመስግኚው
      እርህራሄው : እጅግ : ብዙ : ነው
      ኦ : ነፍሴ : እባክሽ
      ፍቅሩን : እያሰብሽ : አመስግኚው
      እርህራሄው : እጅግ : ብዙ : ነው

ለቁጣው : የዘገየ : ፍቅሩም : የበዛ : አምላክ : ነውና
ለሚፈሩት : ሁሉ : የምህረት : አምላክ : ነው : የእንደገና
ምስራቅ : ከምዕራብ : እንደሚርቅ : መጠን
ከአንቺ : አስወገደው : የሚያስጨንቅሽን

እንደ : ሚራራ : አባት ለውድ : ልጆቹ
ዘወትር : የያዘሽ : በሰፊው : እጆቹ
ነፍሴ : ሆይ : አስቢ : ታላቅ : ውለታውን
ሁልጊዜ : አፍልቂ : ለርሱ : ሚገባውን

   አዝ፦ ኦ : ነፍሴ : እባክሽ
      ምህረቱን : እያሰብሽ : አመስግኚው
      እርህራሄው : እጅግ : ብዙ : ነው
      ኦ : ነፍሴ : እባክሽ
      ፍቅሩን : እያሰብሽ : አመስግኚው
      እርህራሄው : እጅግ : ብዙ : ነው

በበረሀው : ምድር : ምንም : በሌለበት
ለጥምሽ : እርካታ : ለድካምሽ : እረፍት
ለጠላት : ፍላጻ : ከቀስተኛም : ትኩረት
ከለላ : የሆነልሽ : ካንቺ : ፍቅር : ይዞት

በለመለመው : መስክ : ዘውትር : እየመራሽ
በጠላትሽም : ፊት : በዘይት : የቀባሽ
እንደ : በደልሽ : ያልከፈለሽ : ምህረቱን : ያበዛልሽ : እግዚአብሔር : ነው
እንደ : በደልሽ : ያልከፈለሽ : ቸርነቱን : ያበዛልሽ : እግዚአብሔር : ነው

ኦ : ነፍሴ : እግዚአብሔርን : ባርኪ : ነፍሴ
ኦ : ነፍሴ : እግዚአብሔርን : ባርኪ : ነፍሴ