From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ዳዊት ጌታቸው (Dawit Getachew)
|
|
፪ (2)
|
አምንሀለው (amnihalehu)
|
ቁጥር (Track):
|
፩ (1)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:46
|
ጸሐፊ (Writer):
|
ዳዊት ጌታቸው (Dawit GetachewProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የዳዊት ጌታቸው ፡ አልበሞች (Albums by Dawit Getachew)
|
|
ክብር ፡ ምስጋና ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሄር
ወዶናልና ፡ ከቶ ፡ ላይተወን ፡ በዘላለም ፡ ፍቅር
ክብር ፡ ምስጋና ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሄር
በእራሱ ፡ ምሏል ፡ ከቶ ፡ ላይተወን ፡ ታላቅ ፡ እርስት ፡ ሆነን
ወድቀን ፡ ሳለን ፡ ተጥለን ፡ስንጨነቅ ፡ ሚረዳን ፡ አተን
በደም ፡ ተለዉሰን ፡ ሳለን ፡ በብዙ ፡ ስቃይ ፡ ተስፋ ፡ ቆርጠን
አይቶ ፡ እጅግ ፡ እራራልን ፡ ቁስላችንን ፡ አጥቦ ፡ ፈወሰን
ልጁን ፡ በወደደበት ፡ ፍቅር ፡ እኛንም ፡ እንዲሁ ፡ ወደደን
አዝ፦ አዳነን ፡ ከጨለማ ፡ ወደሚደነቅ ፡ ብርሃኑም ፡ ጠራን
የእርሱን ፡ ፍቅር ፡ በጎነት ፡ እንድንናገር ፡ ተመረጥን
ታላቅ ፡ ህዝብ ፡ አደረገን ፡ የተለየን ፡ የንጉስ ፡ ካህን
ምህረትን ፡ አግኝተን ፡ ተባልን ፡ የእግዚአብሄር ፡ ወገን
ወገን /3/ ወገን : አደረገን
ልጆች /3/ ልጆቹ : አረገን
አፀደቀን...
አምላክ ፡ ተብሎ ፡ ሊጠራብን ፡ እግዚአብሄር ፡ ስላላፈረብን
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አብረን ፡ እንድንኖር ፡ በሰማይ ፡ ስፍራ ፡ አዘጋጀልን
ወደደን ፡ ደግሞም ፡ አፀደቀን ፡ ከእንግዲ ፡ ማነው ፡ ሚኮንነን
ሰቶናል ፡ የልጅነት ፡ መንፈስ ፡ እንድንጠራው ፡ አብ ፡ አባት ፡ ብለን
አዝ፦ አዳነን ፡ ከጨለማ ፡ ወደሚደነቅ ፡ ብርሃኑም ፡ ጠራን
የእርሱን ፡ ፍቅር ፡ በጎነት ፡ እንድንናገር ፡ ተመረጥን
ታላቅ ፡ ህዝብ ፡ አደረገን ፡ የተለየን ፡ የንጉስ ፡ ካህን
ምህረትን ፡ አግኝተን ፡ ተባልን ፡ የእግዚአብሄር ፡ ወገን
ወገን /3/ ወገን : አደረገን
ልጆች /3/ ልጆቹ : አረገን
አፀደቀን...
|