አንተ ክብሬ ነህ (Ante Kibre Neh) - ዳዊት ጌታቸው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Lyrics.jpg


(2)

አልበም
(Amnihalehu)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

ይሄ ቢሆንልኝ ብዬ ምመኘው
ህልሜ እውን ሆኖ መች ነው የማየው
ብዬ የማስበው የማልመው ነገር
ተሰቶኛል አንተን ያገኝው ቀን።

ተራራ አልጣው ወይ አልወረድኩ
ግን እንዲሁ በጸጋ ስለወደድከኝ
ከምገምትውና ከማሰበው በላይ
ቤት ሰርተህልኛል በሰማይ
ከምገምትውና ከማሰበው በላይ
ቤት ሰርተህልኛል በሰማይ

አንተ ክብሬ ነህ አንተ ጥበቤ
ቅድስናዬ የሱስ በዛዬ
ምን አለኝ የምሻው ከንግዲ
ሁሉ ተሰቶኛል በስምህ
ፍቅርህን እያሰብኩ
ሁሌ አመልክሃልሁ
የእግዚያብሔር ልጅ ወድሃልሁ

አሁን ያንተ የሆነው ሁሉ የኔ ነው
ፍለጋ አልሄድም
ማዶ ማዶ እያየሁ
የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠህኝ
ካንተ የተነሳ
የእግዚያብሔር ልጅ ነኝ
የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠህኝ
ካንተ የተነሳ
የንጉስ ልጅ ነኝ

አንተ ክብሬ ነህ አንተ ጥበቤ
ቅድስናዬ የሱስ በዛዬ
ምን አለኝ የምሻው ከንግዲ
ሁሉ ተሰቶኛል በስምህ
ፍቅርህን እያሰብኩ
ሁሌ አመልክሃልሁ
የእግዚያብሔር ልጅ ወድሃልሁ
ነጻ ወጥቻለሁ
ከሃጢያት አበሳ
ባርነቴ ቀርቶል
ካንተ የተነሳ
አንተ መሃል ገብተህ
እኔን አስመለጥከኝ
ውርደቴን ስድቤን
ሞቴን ወሰድክልኝ (ኦኦኦኦኦ)
ነጻ ወጥቻለሁ
ከሃጢያት አበሳ
ባርነቴ ቀርቶል
ካንተ የተነሳ
አንተ መሃል ገብተህ
እኔን አስመለጥከኝ
ውርደቴን ስድቤን
ሞቴን ወሰድክልኝ

የሱስ ኩራቴ ቅድስናዬ
የሱስ ትምክቴ
ምን አለኝ የምሻው ከንግዲህ
ሁሉ ተሰቶኛል በስምህ
ፍቅርህን እያሰብኩ
ሁሌ አመልክሃልሁ
የእግዚያብሔር ልጅ ወድሃልሁ