From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ስፀልይ ፡ ነፍሴ ፡ ይነቃቃል
ስፀልይ ፡ እንባዬም ፡ ይደርቃል
ስፀልይ ፡ ሁሌ ፡ እበረታለሁ
ስፀልይ ፡ ኃይልን ፡ አገኛልሁ
ስፀልይ ፡ ቋጠሮ ፡ ይፈታል
ስፀልይ ፡ መዝጊያው ፡ ይከፈታል
ስፀልይ ፡ ሁሌ ፡ እጽናናለሁ
ስፀልይ ፡ እረፍት ፡ አገኛለሁ
ስፀልይ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ይወድቃል
ስፀልይ ፡ ስፍራውን ፡ ይለቃል
ስፀልይ ፡ ድልን ፡ አገኛለሁ
ስፀልይ ፡ ሀሴት ፡ አደርጋለሁ
ስፀልይ ፡ ቃሉን ፡ እረዳለሁ
ስፀልይ ፡ አስተውለዋለሁ
ስፀልይ ፡ እምነት ፡ እሞላለሁ
ስፀልይ ፡ ሁሌ ፡ እደሰታለሁ
ለአንድ ፡ ክርስቲያን ፡ በኢየሱስ ፡ ለዳነ
የዘለዓለምን ፡ ሕይወትን ፡ ላገኛ
ጸሎት ፡ ትልቁ ፡ ዋና ፡ ለሕይወቱ
ትልቁ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ቁልፉ
ጸሎት ፡ ትልቁ ፡ ዋና ፡ ለሕይወቱ
ትልቁ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ቁልፉ (፪x)
ስኖር ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ በዚህች ፡ ምድር ፡ ላይ
እንዴት ፡ ሳልጸልይ ፡ የሱን ፡ ፊት ፡ ሳላይ
ድምጼን ፡ ሳሰማው ፡ ድምጹን ፡ ሲያሰማኝ
ጸሎት ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ያስተማረኝ
ድምጼን ፡ ሳሰማው ፡ ድምጹን ፡ ሲያሰማኝ
ጸሎት ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያስተማረኝ (፪x)
በቃሉ ፡ ነግሮኝ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ጩህ ፡ ብሎ
መልስ ፡ እንዲሰጠኝ ፡ በእራሱ ፡ ምሎ
እኔም ፡ በፊቱ ፡ ተንበረከኩኝ
ታላቅ ፡ እንዳለኝ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አየሁኝ
በሬን ፡ ዘግቼው ፡ በስውር ፡ ለምኜው
በግልጽ ፡ ከፍሎኛል ፡ ጌታን ፡ ታምኜው (፪x)
አዝ፦ ስፀልይ ፡ ነፍሴ ፡ ይነቃቃል
ስፀልይ ፡ እንባዬም ፡ ይደርቃል
ስፀልይ ፡ ሁሌ ፡ እበረታለሁ
ስፀልይ ፡ ኃይልን ፡ አገኛልሁ
ስፀልይ ፡ ቋጠሮ ፡ ይፈታል
ስፀልይ ፡ መዝጊያው ፡ ይከፈታል
ስፀልይ ፡ ሁሌ ፡ እጽናናለሁ
ስፀልይ ፡ እረፍት ፡ አገኛለሁ
ስፀልይ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ይወድቃል
ስፀልይ ፡ ስፍራውን ፡ ይለቃል
ስፀልይ ፡ ድልን ፡ አገኛለሁ
ስፀልይ ፡ ሀሴት ፡ አደርጋለሁ
ስፀልይ ፡ ቃሉን ፡ እረዳለሁ
ስፀልይ ፡ አስተውለዋለሁ
ስፀልይ ፡ እምነት ፡ እሞላለሁ
ስፀልይ ፡ ሁሌ ፡ እደሰታለሁ
|