From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ የማመልከው (፫x)
አታልቅስ ፡ ብሎ ፡ ከሃዘኔ ፡ ያጽናናኝ
ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ ያበረታኝ (፪x)
መጽሃፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ የሆነው ፡ አንበሳ
ገናናው/ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x)
ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አዎ
ቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አሜን
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x)
መለከት ፡ ይነፋ ፡ ይወራለት ፡ ዝናው
አዋጁም ፡ ይታወጅ ፡ እንዳይኖር ፡ ያልሰማ
ሞት ፡ መውጊያው ፡ ተሰብሮ ፡ ጉልበቱ ፡ ደቀቀ
ሲኦል ፡ ተሸነፈ ፡ ቁልፉ ፡ ተነጠቀ
ይህን ፡ ማድረግ ፡ የቻለ ፡ ከኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ማነው
አያንስበትም ፡ ወይ ፡ ታድያ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ባመልከው
ይህን ፡ ላደረገው ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ስለሚገባው
አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት
ይድመቅ ፡ ዕልልታው ፡ ስለሚገባው (፬x)
የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ የማመልከው (፫x)
አታልቅስ ፡ ብሎ ፡ ከሃዘኔ ፡ ያጽናናኝ
ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ ያበረታኝ (፪x)
መጽሃፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ የሆነው ፡ አንበሳ
ገናናው/ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x)
ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አዎ
ቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አሜን
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x)
ጌታዎች ፡ ባርያዎች ፡ ድሆች ፡ ባለጸጋዎች
ታናናሽ ፡ ታላላቅ ፡ ሃያላን ፡ ደካሞች
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ የሚምበረከክለት
ሕያውም ፡ ግዑዙም ፡ የሚንቀጠቀጥለት
እረ ፡ እንዴት ፡ ምስጉን ፡ ነው ፡ ወዶ ፡ የሚያመልከው
በዕልልታ ፡ በሆታ ፡ ስሙን ፡ ያወደሰው
ይህን ፡ ላደረገው ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ስለሚገባው
አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት
ይድመቅ ፡ ዕልልታው ፡ ስለሚገባው (፬x)
|