From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃለሁ (፪x)
የማይገባኝን ፡ እኔን ፡ ያስወደደህ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞተህ ፡ ነፍስህን ፡ ለእኔ ፡ ሰጠህ
መቼ ፡ ይረሳኛል ፡ ሁሌ ፡ አስበዋለሁ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ አመሰግናለሁ
አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃለሁ (፪x)
በማይለወጥ ፡ ፍቅር ፡ እኔን ፡ ወደኸኛል
ለክብርህ ፡ እንዳጥን ፡ አንተ ፡ መርጠኸኛል
ሳልሰለች ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ
ለዘለዓለሙ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃለሁ
አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃለሁ (፪x)
በእኔ ፡ ዘንድ ፡ ያለ ፡ በአንተ ፡ ዝንድ ፡ የሌለ
ያለ ፡ ነገር ፡ ቢኖር ፡ እሰጥህ ፡ ነበረ
አንተ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነህ
ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ ምሥጋና ፡ ለሥምህ
አዝ፦ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃለሁ (፪x)
አስብህና ፡ እደሰታለሁ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እወድሃለሁ
አስብህና ፡ እደሰታለሁ ፡ የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ እወድሃለሁ
አስብህና ፡ እፎይ ፡ እላለሁ ፡ የእረፍቴ ፡ እወድሃለሁ
አስብህና ፡ እኔ ፡ እርፋለሁ ፡ የእረፍቴ ፡ እወድሃለሁ
አስብህና ፡ እደሰታለሁ ፡ የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ወድሃለሁ
አስብህና ፡ እደሰታለሁ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ እወድሃለሁ
|