ማነው ፡ እንደ ፡ ኖህ (Manew Ende Noh) - ቢኒያም ፡ መኮንን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቢኒያም ፡ መኮንን
(Biniyam Mekonnen)

Lyrics.jpg


(2)

ፍቅርህ ፡ ነው ፡ የያዘኝ
(Feqreh New Yeyazegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢኒያም ፡ መኮንን ፡ አልበሞች
(Albums by Biniyam Mekonnen)

ዳዊት ፡ በዮናታን ፡ ዮናታን ፡ በዳዊት
ፍቅር ፡ ሲጀምር ፡ በነገስታት ፡ ቤት
በነፍስ ፡ ሲታሰር ፡ የፍቅር ፡ ኪዳን
አይለዋወጥ ፡ ፌዝ ፡ የለም ፡ ነበር

ሳኦል ፡ ሊገድለው ፡ ሲሻ ፡ ዳዊት
ያስመልጥ ፡ ነበር ፡ ቅን ፡ ዮናታን
የፍቅር ፡ ትርጉም ፡ ሲገባኝ ፡ እኔ
አንድ ፡ አላየሁም ፡ በዚህ ፡ ዘመኔ

ትናንት ፡ ሰው ፡ ሲሆን ፡ የወደድኩት
ዛሬ ፡ ኣውሬ ፡ ሆኖ ፡ ባይኔ ፡ አየሁት
ማታ ፡ በፍቅር ፡ የማለልኝ
ጠዋት ፡ ሰማሁት ፡ ሲዝትብኝ
ሲለዋወጥስ ፡ የጉራማይሌ
እጅጉን ፡ አዘንኩ ፡ ሲረሳ ፡ አምላኬ

አዬ ፡ ክርስትናዬ

ማነው ፡ እንደ ፡ ኖህ ፡ ኣለምን ፡ በጽድቁ ፡ የኮነነው
ኣንደበቱ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ህይወቱ ፡ የሚያወራው
በፍርድ ፡ ሚዛን ፡ ላይ ፡ ራሱን ፡ አስቀምጦ
ወንድሙን ፡ የሚያርድ ፡ በዝቶአል ፡ ከቃሉ ፡ አብልጦ
አታርገው ፡ ባዳ ፡ ኣታርገው ፡ ከንቱ
እቀፈው ፡ እንጂ ፡ እንደበፊቱ
ደም ፡ የፈሰሰው ፡ ቀራንዮ ፡ ላይ
ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አንለያይ

አንለያይ!

ኧረ ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ አልከን
ስንበላላ ፡ ስንነካከስ ፡ ስንጨራረስ ፡ ጌታችን
ምን ፡ ትለን ፡ ይሆን ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ አልከን (፪x)

ቀንና ፡ ሌሊት ፡ መልካም ፡ አሳቢ
ለክፉ ፡ ነገር ፡ መልሱ ፡ ነው ፡ እምቢ
ዘመኑን ፡ ሙሉ ፡ ደግ ፡ እየኖረ
ፍቅር ፡ ሰባኪ ፡ ለእውነት ፡ ያደረ

ግን ፡ ይገርመኛል ፡ የዚህ ፡ ሰው ፡ ሕይወት
ምድር ፡ መከራ ፡ ጭንቅ ፡ የሆነችበት
ለእውነት ፡ ባደረ ፡ ምላሹ ፡ ሌላ
ምነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ሚገፋው ፡ በዛ

አይሳመው ፡ እንጂ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ይሁዳ
ያሴርበታል ፡ ሄዶ ፡ ከጓዳ
መንገዱ ፡ ቢመስል ፡ ውሎው ፡ ከጌታ
ልቡ ፡ ዴማስ ፡ ነው ፡ ሲገለጥ ፡ ማታ

አዬ! ፡ ክርስትናዬ!

ዘመኑን ፡ ሙሉ ፡ ቤቱ ፡ አገልግሎ
በታማኝነት ፡ አምላኩን ፡ ብሎ
ደፋ ፡ ቀና ፡ ሲል ፡ ሰጥቶ ፡ ሕይወቱን
ድንገት ፡ ወደቀ ፡ ጥሎ ፡ ብርታቱን

በኃይሉ ፡ ጊዜ ፡ ያላነሱት
ዛሬ ፡ ሲወድቅ ፡ አስታወሱት
ከሰገባቸው ፡ ሰይፋቸው ፡ ወጣ
የትናንት ፡ ድካም ፡ ሁሉ ፡ እስኪረሳ

እንዳይመለስ ፡ እግዜሩን ፡ ፈርቶ
ወንድሙ ፡ ቆሞኣል ፡ ቢላውን ፡ ስሎ
ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ይመለስ
ፍርድ ፡ ካልመጣ ፡ ከሰማይ ፡ መቅደስ

አዬ! ፡ ክርስትናዬ!!