ቢኒያም ፡ መኮንን (Biniyam Mekonnen) - ነጠላ (Single)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቢኒያም ፡ መኮንን
(Biniyam Mekonnen)

Cds.jpg

' ነጠላ
(Single)
ዓ.ም. (Year):
ለመግዛት (Buy):
የቢኒያም ፡ መኮንን ፡ አልበሞች
(Albums by Biniyam Mekonnen)
፩) ናና አረስርሰኝ (Nana Aresrsegn) 10:10













ዛሬን ፈለኩህ እንደገና ናፈኩ

ዛሬን ፈለኩህ እየሱስዬ ተራብኩ

ዛሬን ፈለኩህ እንደገና ናፈኩ

ዛሬን ፈለኩህ የኔ ፍቅር ተራብኩ


ናና አረስርሰኝ (፬x)


ዛሬን ፈለኩህ እንደገና ናፈኩ

ዛሬን ፈለኩህ እየሱስዬ ተራብኩ

ዛሬን ፈለኩህ እንደገና ናፈኩ

ዛሬን ፈለኩህ የኔ ወዳጅ ተራብኩ


ናና አረስርሰኝ (፬x)


ክብርህ ክብርህ ክብርህ ናፈቀኝ

ያንተ ህልውና እጅግ ራበኝ


ናና አረስርሰኝ (፬x)


የተማሰው ጉድጉዋድ አፉ በእኔ ላይ አልዘጋም

ጉልበቴ ባለቀ ጊዜ ለብቻዬ አልተውከኝም

ስለትንሿዋ እምነቴ ከባለጋራ ጋር ተሟግተክ

የድል አንባን አስረገጥክኝ ውጊያዬ ሁሉ ፈጸመህ


እጅግ ተቸግሬ ስማጸን አይተኸኝ

እኔ ካንተ ጋር ነኝ አትፍራ ያልከኝ

በመጸናናት ሞልተክ ደስታን ታስታጥቀኛለህ

የልቤ አምላክ ሆይ ለዘላለም እድልፈንታዬ ነህ


ምስጋናዬን እያዜምኩኝ ባንተ ደስ ይለኛል

በከንቱ በሚጠሩህ ፊት ሞገስ አጎናጽፈኸኛል

አለም ብትሰርዘኝም የህይወት መዝገብ አውቆኛል

እስከመጨረሻው ድረስ ህይወቴ ባንተ ይጸናል


እጅግ ተቸግሬ ስማጸን አይተኸኝ

እኔ ካንተ ጋር ነኝ አትፍራ ያልከኝ

በመጸናናት ሞልተክ ደስታን ታስታጥቀኛለህ

የልቤ አምላክ ሆይ ለዘላለም እድልፈንታዬ ነህ


እግዚአብሄር ይሄ ነው ተስፋ ያደረኩት

ታማኝነቱን አይቼ እጄን ልቤን የሰጠሁት

ያላዋቂዎች ልቦና በሰዎች ተስፋ ያደርጋል

ግን እየሱስዬ ብቻ ደንነትን ያዘጋጃል


እጅግ ተቸግሬ ስማጸን አይተኸኝ

እኔ ካንተ ጋር ነኝ አትፍራ ያልከኝ

በመጸናናት ሞልተክ ደስታን ታስታጥቀኛለህ

የልቤ አምላክ ሆይ ለዘላለም እድልፈንታዬ ነህ


አንተ ብሩክ ምንጭ ነህ (፬x)

ነፍስን የምታረካ ልብን የምትመልስ

አንተ የሰላም ንጉሥ ነህ

አንተ የሰላም አባት (፪x)


ሁለተኛ እንዳልጠማ

አረካኸኝ ከሕይወት ውሃ

አንተ ሕይወት መንገድ ሆንክልኝ

በብርሃኔ ብርሃን አሳየኸኝ


አከብርሃለሁ ክበር (፫x)

ክብር ለአንተ ይሁን (፪x)