፪ኛ ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች - ምዕራፍ ፪ (2nd Thesallonians - Chapter 2)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


፩፡ ነገር ፡ ግን ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ ስለ ፡ ጌታችን ፡ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ መምጣትና ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ስለ ፡ መሰብሰባችን ፥ በመንፈስ ፡ ወይም ፡ በቃል ፡ ወይም ፡ ከእኛ ፡ እንደሚመጣ ፡ በመልእክት። የጌታ ፡ ቀን ፡ ደርሶአል ፡ ብላችሁ ፥ ከአእምሮአችሁ ፡ ቶሎ ፡ እንዳትናወጡ ፡ እንዳትደነግጡም ፡ እንለምናችኋለን። ፪፡ ማንም ፡ በማናቸውም ፡ መንገድ ፡ አያስታችሁ ፤ ክህደቱ ፡ አስቀድሞ ፡ ሳይመጣና ፡ የዓመፅ ፡ ሰው ፡ እርሱም ፡ የጥፋት ፡ ልጅ ፡ ሳይገለጥ ፥ አይደርስምና። ፫፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነኝ ፡ ብሎ ፡ አዋጅ ፡ እየነገረ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቤተ ፡ መቅደስ ፡ እስኪቀመጥ ፡ ድረስ ፥ አምላክ ፡ ከተባለው ፡ ሁሉ ፥ ሰዎችም ፡ ከሚያመልኩት ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ራሱን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ የሚያደርገው ፡ ተቃዋሚ ፡ እርሱ ፡ ነው። ፬፡ ገና ፡ ከእናንተ ፡ ጋር ፡ ሳለሁ ፥ ይህን ፡ እንዳልኋችሁ ፡ ትዝ ፡ አይላችሁምን ? ፭፡ በገዛ ፡ ራሱ ፡ ጊዜም ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፥ የሚከለክለውን ፡ አሁን ፡ ታውቃላችሁ። ፮፡ የዓመፅ ፡ ምሥጢር ፡ አሁን ፡ ይሠራልና ፤ ብቻ ፡ ከመንገድ ፡ እስኪወገድ ፡ ድረስ ፡ አሁን ፡ የሚከለክል ፡ አለ። ፯፡ በዚያም ፡ ጊዜ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በአፉ ፡ መንፈስ ፡ የሚያጠፋው ፥ ሲመጣም ፡ በመገለጡ ፡ የሚሽረው ፡ ዓመፀኛ ፡ ይገለጣል ፤ ፰፡ ይድኑ ፡ ዘንድ ፡ የእውነትን ፡ ፍቅር ፡ ስላልተቀበሉ ፡ ለሚጠፉ ፥ የእርሱ ፡ መምጣት ፡ በተአምራት ፡ ሁሉና ፡ በምልክቶች ፡ በሐሰተኞች ፡ ድንቆችም ፡ በዓመፅም ፡ መታለል ፡ ሁሉ ፡ እንደ ፡ ሰይጣን ፡ አሠራር ፡ ነው። ፱፡ ስለዚህም ፡ ምክንያት ፥ በእውነት ፡ ያላመኑ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ በዓመፅ ፡ ደስ ፡ ይላቸው ፡ የነበሩ ፡ ሁሉ ፡ ፍርድን ፡ እንዲቀበሉ ፥ ሐሰትን ፡ ያምኑ ፡ ዘንድ ፡ እግዚአብሔር ፡ የስሕተትን ፡ አሠራር ፡ ይልክባቸዋል። ፲፡ እኛ ፡ ግን ፥ በጌታ ፡ የተወደዳችሁ ፡ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ ሁልጊዜ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ልናመሰግን ፡ ግድ ፡ አለብን ፥ እግዚአብሔር ፡ በመንፈስ ፡ መቀደስ ፡ እውነትንም ፡ በማመን ፡ ለመዳን ፡ እንደ ፡ በኵራት ፡ መርጦአችኋልና ፤ ፲፩፡ ለዚህም ፡ የጌታችንን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስን ፡ ክብር ፡ ለማግኘት ፡ በወንጌላችን ፡ ጠራችሁ። ፲፪፡ እንግዲያስ ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ ጸንታችሁ ፡ ቁሙ ፥ በቃላችንም ፡ ቢሆን ፡ ወይም ፡ በመልእክታችን ፡ የተማራችሁትን ፡ ወግ ፡ ያዙ። ፲፫፡ ራሱ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስና ፡ የወደደን ፡ በጸጋም ፡ የዘላለምን ፡ መጽናናት ፡ በጎንም ፡ ተስፋ ፡ የሰጠን ፡ እግዚአብሔር ፡ አባታችን ፡ ልባችሁን ፡ ያጽናኑት ፡ በበጎም ፡ ሥራና ፡ በቃል ፡ ሁሉ ፡ ያጽኑአችሁ።















Navigation menu

MediaWiki spam blocked by CleanTalk.