፪ኛ ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች - ምዕራፍ ፪ (2nd Thesallonians - Chapter 1)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


፩፡ ጳውሎስና ፡ ስልዋኖስ ፡ ጢሞቴዎስም ፥ በእግዚአብሔር ፡ በአባታችን ፡ በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስም ፡ ወደምትሆን ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፤ ፪፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከአባታችን ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ክርስቶስም ፡ ጸጋ ፡ ሰላምም ፡ ለእናንተ ፡ ይሁን። ፫፡ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ እምነታችሁ ፡ እጅግ ፡ ስለሚያድግ ፡ የሁላችሁም ፡ የእያንዳንዳችሁ ፡ ፍቅር ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ ስለሚበዛ ፥ ሁልጊዜ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ እግዚአብሔርን ፡ እንደሚገባ ፡ ልናመሰግን ፡ ግድ ፡ አለብን ፤ ፬፡ ስለዚህ ፡ በምትታገሱበት ፡ በስደታችሁና ፡ በመከራችሁ ፡ ሁሉ ፡ ከመጽናታችሁና ፡ ከእምነታችሁ ፡ የተነሣ ፡ በእግዚአብሔር ፡ አብያተ ፡ ክርስቲያናት ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ ራሳችን ፡ እንመካለን። ፭፡ ስለ ፡ እርሱ ፡ ደግሞ ፡ መከራ ፡ ለምትቀበሉለት ፡ ለእግዚአብሔር ፡ መንግሥት ፡ የምትበቁ ፡ ሆናችሁ ፡ ትቈጠሩ ፡ ዘንድ ፥ ይህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቅን ፡ ፍርድ ፡ ምልክት ፡ ነው። ፮፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሥልጣኑ ፡ መላእክት ፡ ጋር ፡ ከሰማይ ፡ በእሳት ፡ ነበልባል ፡ ሲገለጥ ፥ መከራን ፡ ለሚያሳዩአችሁ ፡ መከራን ፥ መከራንም ፡ ለምትቀበሉ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ዕረፍትን ፡ ብድራት ፡ አድርጎ ፡ እንዲመልስ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ በእርግጥ ፡ ጽድቅ ፡ ነውና። ፯፡ እግዚአብሔርን ፡ የማያውቁትን ፥ ለጌታችንም ፡ ለኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ወንጌል ፡ የማይታዘዙትን ፡ ይበቀላል ፤ ፰፡ በዚያም ፡ ቀን ፡ በቅዱሳኑ ፡ ሊከብር ፥ ምስክርነታችንንም ፡ አምናችኋልና ፡ በሚያምኑት ፡ ሁሉ ፡ ዘንድ ፡ ሊገረም ፡ ሲመጣ ፥ ከጌታ ፡ ፊት ፡ ከኃይሉም ፡ ክብር ፡ ርቀው ፡ በዘላለም ፡ ጥፋት ፡ ይቀጣሉ። ፱፡ ስለዚህም ፡ ደግሞ ፡ እንደ ፡ አምላካችን ፡ እንደ ፡ ጌታም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ጸጋ ፥ የጌታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም ፡ በእናንተ ፡ ዘንድ ፡ ሊከብር ፡ እናንተም ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ልትከብሩ ፥ አምላካችን ፡ ለመጥራቱ ፡ የምትበቁ ፡ አድርጎ ፡ ይቈጥራችሁ ፡ ዘንድ ፥ የበጎነትንም ፡ ፈቃድ ፡ ሁሉ ፡ የእምነትንም ፡ ሥራ ፡ በኃይል ፡ ይፈጽም ፡ ዘንድ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ ሁልጊዜ ፡ እንጸልያለን።

















Navigation menu

MediaWiki spam blocked by CleanTalk.