፩ኛ ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች - ምዕራፍ ፩ (1st Thesallonians - Chapter 1)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


፩፡ ጳውሎስና ፡ ስልዋኖስ ፡ ጢሞቴዎስም ፥ በእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስም ፡ ወደምትሆን ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፤ ከእግዚአብሔር ፡ ከአባታችን ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ክርስቶስም ፡ ጸጋ ፡ ሰላምም ፡ ለእናንተ ፡ ይሁን። ፪፡ በጸሎታችን ፡ ጊዜ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ ስናሳስብ ፥ የእምነታችሁን ፡ ስራ ፡ የፍቅራችሁንም ፡ ድካም ፡ በጌታችንም ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ያለውን ፡ የተስፋችሁን ፡ መጽናት ፡ በአምላካችንና ፡ በአባታችን ፡ ፊት ፡ ሳናቋርጥ ፡ እያሰብን ፥ እግዚአብሔርን ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ በሁላችሁ ፡ ምክንያት ፡ እናመሰግናለን ፤ ፫፡ በእግዚአብሔር ፡ የምትወደዱ ፡ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ እንደ ፡ ተመረጣችሁ ፡ አውቀናልና። ፬፡ ወንጌላችን ፡ በኃይልና ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በብዙ ፡ መረዳትም ፡ እንጂ ፡ በቃል ፡ ብቻ ፡ ወደ ፡ እናንተ ፡ አልመጣምና ፤ በእናንተ ፡ ዘንድ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ እንዴት ፡ እንደ ፡ ነበርን ፡ ታውቃላችሁ። ፭፡ ደግሞ ፡ እናንተ ፡ ቃሉን ፡ በብዙ ፡ መከራ ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ደስታ ፡ ጋር ፡ ተቀብላችሁ ፥ እኛንና ፡ ጌታን ፡ የምትመስሉ ፡ ሆናችሁ ፤ ፮፡ ስለዚህም ፡ በመቄዶንያና ፡ በአካይያ ፡ ላሉት ፡ ምእመናን ፡ ሁሉ ፡ ምሳሌ ፡ ሆናችሁላቸው። ፯፡ ከእናንተ ፡ ወጥቶ ፡ የጌታ ፡ ቃል ፡ በመቄዶንያና ፡ በአካይያ ፡ ብቻ ፡ አልተሰማምና ፥ ነገር ፡ ግን ፡ ምንም ፡ እንድንናገር ፡ እስከማያስፈልግ ፡ ድረስ ፥ በእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ የሚሆን ፡ እምነታችሁ ፡ በሁሉ ፡ ስፍራ ፡ ተወርቶአል። ፰፡ እነርሱ ፡ ራሳቸው ፡ ወደ ፡ እናንተ ፡ መግባታችን ፡ እንዴት ፡ እንደነበረ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ ይናገራሉና ፤ ለሕያውና ፡ ለእውነተኛ ፡ አምላክም ፡ ታገለግሉ ፡ ዘንድ ፥ ከሙታንም ፡ ያስነሳውን ፡ ልጁን ፡ እርሱንም ፡ ኢየሱስን ፡ ከሚመጣው ፡ ቍጣ ፡ የሚያድነንን ፡ ከሰማይ ፡ ትጠብቁ ፡ ዘንድ ፥ ከጣዖቶች ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዴት ፡ ዘወር ፡ እንዳላችሁ ፡ ይናገራሉ።


















Navigation menu

MediaWiki spam blocked by CleanTalk.