ይህን ፡ ያረገው (Yehen Yaregew) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

ወደ ፡ ፀጋህ ፡ ዙፋን ፡ በእምነትህ ፡ እቀርባለሁ ፤ በእምነትህ ፡ እቀርባለሁ
በኢየሱስ ፡ ምክንያት ፡ ድፍረት ፡ አግኝቻለሁ ፤ ድፍረት ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

የከበደው ፡ ኪዳን ፡ ይኸው ፡ ቀለለልኝ ፤ ይኸው ፡ ቀለለልኝ
በነጻ ፡ እንዳመልከው ፡ ልጁን ፡ ሰደደልኝ ፤ ልጁን ፡ ሰደደልኝ (፪x)

ይህን ፡ ያረገው (፪x) ፡ ይህን ፡ ያረገው ፡ ጌታዬ ፡ እንዳመልከው ፡ ነው
ይህን ፡ ያረገው (፪x) ፡ ይህን ፡ ያረገው ፡ ጌታዬ ፡ እንዳመልከው ፡ ነው

በግ : እርግብ ፡ አልይዝም ፡ አንተን ፡ ለማምለክ ፤ አንተን ፡ ለማምለክ
እንጨት ፡ ረብርቤ ፡ እሳት ፡ አላነድም ፤ እሳት ፡ አላነድም (፪x)

ያንን ፡ ከባድ ፡ ስርዓት ፡ ኢየሱስ ፡ አስቀረው ፤ ጌታዬ ፡ አስቀረው
ያለምንም ፡ ድካም ፡ እርሱን ፡ እንዳመልከው ፤ እርሱን ፡ እንዳመልከው ፡ አዎ (፪x)

ይህን ፡ ያረገው (፪x) ፡ ይህን ፡ ያረገው ፡ ጌታዬ ፡ እንዳመልከው ፡ ነው
ይህን ፡ ያረገው (፪x) ፡ ይህን ፡ ያረገው ፡ ጌታዬ ፡ እንዳመልከው ፡ ነው

በፍፁም ፡ ልቤ ፡ በፍፁም ፡ ሃሳቤ
ጌታን ፡ እወደዋለሁ ፡ ከሁሉም ፡ አብልጬ (፪x)
አብልጬ ፡ ከሁሉም ፡ አስበልጬ (፰x)