From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ይህም ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ያልፋል ፤ ያልፋል
ያልፋል ፡ ሃዘን ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ደስታም ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ያልፋል ፤ ያልፋል
የማታልፍ ፡ ጌታ ፡ ሁሌ ፡ ያው ፡ የሆንክ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጸንተህ ፡ ምትኖር (፪x)
ዞር ፡ ብዬ ፡ አሰብኩትና ፡ ያለፍኩትን ፡ ብዙ ፡ ጐዳና
ቀና ፡ ብዬ ፡ አንተን ፡ ግን ፡ ሳይ
አላልፈክም ፡ እኮ ፡ ያው ፡ በዙፋንህ
ያው ፡ በዙፋንህ ፡ ጌታዬ ፡ ያው
በዙፋንህ ፡ አሃ/ኦሆ (፪x)
ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ይህም ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ያልፋል ፤ ያልፋል
ያልፋል ፡ ሃዘን ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ደስታም ፡ ያልፋል
ያልፋል ፡ ሁሉም ፡ ያልፋል ፤ ያልፋል
የማታልፍ ፡ ጌታ ፡ ሁሌ ፡ ያው ፡ የሆንክ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጸንተህ ፡ ምትኖር (፪x)
ከንፈሬን ፡ አልከለክልም ፡ አንደበቴ ፡ ለአንተ ፡ ዝም ፡ አይልም
ከልቤ ፡ አከብረዋለሁ ፡ ፈቅጄም ፡ አመልክሃለሁ
ክብር ፡ ለአንተ (ኦሆሆሆ) ፡ ሞገስ ፡ ለአንተ (አሃሃሃ) ፡ ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ነው
ምሥጋና ፡ ለአንተ (ኦሆሆሆ) ፡ ክብር ፡ ለአንተ (አሃሃሃ) ፡ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ነው
የማመልከው ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው
ሁሉን ፡ በሥልጣኑ ፡ የሚያስተዳድረው
ባለዝና ፡ ሥሙ ፡ የተፈራ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ገናና
ዛሬም ፡ ገናና ፡ ኦሆ ፡ ዛሬም ፡ ገናና ፡ አሃ (፪x)
ገናና ፡ ነው ፤ ገናና ፡ ነው
ገናና ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ገናና ፡ ነው
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሥሙ ፡ የተፈራ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ገናና (፪x)
ገናና ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ገናና ፡ ነው
ገናና ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ገናና ፡ ነው
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሥሙ ፡ የተጠራ/የተፈራ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ገናና (፪x)
|