ወጀቡ (Wejebu) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 7:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

አንተን ፡ የታመነ ፡ መች ፡ አፈረ
አንተን ፡ የታመነ ፡ መች ፡ ከሰረ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ብርቱ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ
ኢየሱሴ ፡ ብርቱ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ብርቱ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ
ኢየሱሴ ፡ ብርቱ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ (፪x)

ትላንትን ፡ አልፌ ፡ ዛሬ ፡ ደርሻለሁ
ደርሻለሁ ፡ ዛሬ ፡ ደርሻለሁ (፪x)
ቀኝህ ፡ ደግፎኛል ፡ ለነገ ፡ አምንሃለሁ
አምንሃለሁ ፡ ለነገ ፡ አምንሃለሁ (፪x)
ምን ፡ ያስደነግጣል ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ
እሰጋለሁ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ (፪x)
ተሻገሪ ፡ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
አምላኬ ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
በኃይሉ ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
በሥራው ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
እኔም ፡ አየሁት ፣ አለ ፡ አለ
ሲደርስልኝ ፣ አለ ፡ አለ
ጠላቴን ፡ ረግጦ ፣ አለ ፡ አለ
ሲወጋልኝ ፣ አለ ፡ አለ

ወጀቡ ፡ ቢበዛ ፡ ነፋሱ ፡ ቢያይልም
ቢያይልም ፡ ነፋሱ ፡ ቢያይልም (፪x)
ቃሉን ፡ እይዛለሁ ፡ አልነቃነቅም
አሃ ፡ አልነቃነቅም (፪x)
ቃል ፡ ይናገር ፡ እንጂ ፡ ቃሉን ፡ የሚጠብቅ
አሃ ፡ ቃሉን ፡ የሚጠብቅ (፪x)
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ ትልቅ
አሃ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ ትልቅ (፪x)

ክበር ፡ ዛሬ ፡ እንደገና (፫x)
ልርካ ፡ ክብርህን ፡ ልይና
ልጥገብ ፡ ክብርህን ፡ ልይና
ልጥገብ ፡ ክብርህን ፡ ልይና (፪x)

ለፈተና ፡ መውጫ ፡ አዘጋጀልኝ
አሃ ፡ አዘጋጀልኝ (፪x)
ለማዕበሉ ፡ ደግሞ ፡ ገደብ ፡ ሰራልኝ
አሃ ፡ ገደብ ፡ ሰራልኝ (፪x)
የእኔ ፡ ነገር ፡ እርሱን ፡ ይመለከተዋል
አሃ ፡ ይመለከተዋል (፪x)
ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋግቶ ፡ አሸንፎልኛል
አሃ ፡ አሸንፎልኛል (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
አምላኬ ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
በኃይሉ ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
በሥራው ፡ አለ ፣ አለ ፡ አለ
እኔም ፡ አየሁት ፣ አለ ፡ አለ
ሲደርስልኝ ፣ አለ ፡ አለ
ጠላቴን ፡ ረግጦ ፣ አለ ፡ አለ
ሲወጋልኝ ፣ አለ ፡ አለ

የዮርዳኖስ ፡ ጩኸት ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ እያጓራ (፫x)
አምላክን ፡ ጥራ ፡ እንጂ ፡ አትደንግጥ ፡ አትፍራ (፫x)
ዮርዳኖስ ፡ ፉከራው ፡ እስክትረግጠው ፡ ነው (፫x)
አይዞህ ፡ በእምነት ፡ ግባ ፡ ያዘዘህ ፡ ጌታ ፡ ነው (፫x)

ክበር ፡ ዛሬ ፡ እንደገና (፫x)
ልርካ ፡ ክብርህን ፡ ልይና
ልጥገብ ፡ ክብርህን ፡ ልይና
ልጥገብ ፡ ክብርህን ፡ ልይና (፫x)