From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ከሆነልኝ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ይልቅ
ያረከው ፡ አንተ ፡ ሆንክልኝ ፡ ድንቅ (፪x)
ስለዚህ ፡ ትበቃኛለህ
ሁልጊዜ ፡ ታስመካኛለህ (፪x)
የከበደኝን ፡ ሁሉ ፡ አንተ ፡ አቀለልከው
ፀሎቴንም ፡ እየሰማህ ፡ ጥያቄዬን ፡ መለስከው
ለሰው ፡ ልጆች ፡ መልካምን ፡ በማድረግ ፡ ደስ ፡ ይልሃል
ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ማንስ ፡ ይመስልሃል
ስለዚህ ፡ ትበቃኛለህ
ሁልጊዜ ፡ ታስመካኛለህ (፪x)
በዕድሌ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ በደረሰኝ ፡ እጣ
ምታኖረኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡ ሁሌ ፡ ባለጠጋ
በክንዶችህ ፡ ተማምኜ ፡ በጥላህ ፡ አድራለሁ
ጥጋቤ ፡ ነህ ፡ እርካታዬ ፡ አርፌብሃለሁ
አዝ፦ ስለዚህ ፡ ትበቃኛለህ
ሁልጊዜ ፡ ታስመካኛለህ (፪x)
በልቤ ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ ሞልቶ ፡ የፈሰሰው (፪x)
በውስጤ ፡ ያረከው ፡ የፍቅር ፡ እሳት ፡ ነው (፪x)
ይህንን ፡ አይቼ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፪x)
በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክልኝ (፫x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ሰጠሁ ፡ እኔ ፡ እቆማለሁ (፪x)
ቸርነት ፡ ምህረትህን ፡ ሁሌ ፡ እናገራለሁ (፪x)
ድብቅ ፡ ጦር ፡ አንስተህ ፡ ጠላቴን ፡ መተሃል (፪x)
ድል ፡ አድራጊው ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል (፪x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክልኝ (፫x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
ታማኝነትህን ፡ ሁሌ ፡ አወራለሁ
ቸርነትህ ፡ ዘለዓለም ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ጌታዬ
ሳከብርህ ፡ ያኔ ፡ ረካለሁ ፡ አምላኬ (፪x)
ታማኝነትህን ፡ ሁሌ ፡ አወራለሁ
ቸርነትህ ፡ ዘለዓለም ፡ ዘምራለሁ (፪x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ጌታዬ
ሳከብርህ ፡ ያኔ ፡ ረካለሁ ፡ አምላኬ (፪x)
|