ራርቶልናል (Rartolenal) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

አዝ፦ እራርቶልናል (፬x)

ቸር ፡ ነውና ፡ መቼ ፡ ይተውናል
ቸር ፡ ነውና ፡ መቼ ፡ ይረሳናል (፪x)
ለረዳን ፡ እንዲህ ፡ ላቆመን (፪x)
በየዕለቱ ፡ ለሚመራን (፪x)
ነፍሳችንን ፡ እያፈሰስን (፪x)
ከእግሮቹ ፡ ሥር ፡ እንሰግዳለን (፪x)

አዝ፦ እራርቶልናል (፬x)

ቸር ፡ ነውና ፡ መቼ ፡ ይተውናል
ቸር ፡ ነውና ፡ መቼ ፡ ይረሳናል (፪x)

ባሕሩንም ፡ በሥልጣን ፡ አዞ (፪x)
ፀጥ ፡ አረገው ፡ በመሃል ፡ ገብቶ (፪x)
ስንጨነቅ ፡ የሚራራልን (፪x)
አባት ፡ አለን ፡ የሚያስብልን (፪x)

እርሱ ፡ ስለ ፡ እኛ/እኔ ፡ ያስባልና ፣ ያስባልና
ተራራውንም ፡ ሜዳ ፡ አድርጓልና ፣ አድርጓልና (፪x)

ዛሬም ፡ አምነዋለሁ
ነገም ፡ አምነዋለሁ
ዘለዓለም ፡ አምነዋለሁ (፪x)

ያስጨነቀኝ ፡ ጠላቴ ፡ አላነቃንቅ ፡ ያለኝ
እየተከታተለ ፡ እረፍትን ፡ የሚነሳኝ
የአምላኬ ፡ ቃል ፡ ሲመጣ ፡ ራርቶ ፡ ዘንበል ፡ ሲልልኝ
ፊቴ ፡ የቆሞው ፡ ተራራ ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ሆነልኝ (፪x)

እርሱ ፡ ስለ ፡ እኛ/እኔ ፡ ያስባልና ፣ ያስባልና
ተራራውንም ፡ ሜዳ ፡ አድርጓልና ፣ አድርጓልና (፪x)

ዛሬም ፡ አምነዋለሁ
ነገም ፡ አምነዋለሁ
ዘለዓለም ፡ አምነዋለሁ (፪x)