ቅዱስ (Qedus) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር (፪x)

በታላቅ ፡ ብርሃን ፡ በክብር ፡ ያለህ
ግርማህ ፡ አስፈሪ ፡ መሳይ ፡ የሌለህ
ፍጥረት ፡ በፊትህ ፡ ይንቀጠቀጣል
ክብርህን ፡ አይቶ ፡ ማን ፡ ሰው ፡ ይቆማል

ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር (፪x)

በፈቃዴ ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ (፬x)

አምላክ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ
ክበር ፡ ጌታ (፬x)
ንጉሥ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ
ንገሥ ፡ ጌታ (፬x)

ስለአንተ ፡ በየዕለቱ ፡ መደነቅ ፡ ሞልቶኛል
ዛሬ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አምልኪው ፡ ይለኛል
ለምን ፡ እንደምኖር ፡ ምክኒያቱ ፡ ገብቶኛል
አንተን ፡ ለማምለክ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ ተስማምቶኛል

በመፍራት ፡ በመንቀጥቀጥ ፡ በፊትህ ፡ እቀርባለሁ
ክብር ፡ ለሚገባህ ፡ ለአንተ ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ
አምላኬ ፡ ይገባሃል ፡ ክብር
አምላኬ ፡ ይገባሃል
አምላኬ ፡ ይገባሃል ፡ ስግደት
አምላኬ ፡ ይገባሃል (፪x)

አምላክ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ
ክበር ፡ ጌታ (፬x)
ንጉሥ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ
ንገሥ ፡ ጌታ (፬x)

አምላክ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ
ክበር ፡ ጌታ (፬x)
ንጉሥ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ
ንገሥ ፡ ጌታ (፬x)