ቃልህን ፡ ወደድኩት (Qalehen Wededkut) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

አዝ፦ ብዙ ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው
በቃልህም ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው
የደስታዬ/የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
መተኪያና ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x)

ቃልህን ፡ እወደዋለሁ (፪x)
ድምጽህን ፡ እወደዋለሁ (፪x)

የእግዚአብሔር ፡ ቃሉ ፡ የነጠረ ፡ ነው
ለሚታመኑበት ፡ እርሱ ፡ ጋሻ ፡ ነው
ለቃልህ ፡ ጌታዬ ፡ እኔም ፡ እገዛለሁ
ሁኚ ፡ ያለኝን ፡ ሁሉ ፡ ዛሬም ፡ እሆናለሁ

ያፅናናኝን ፡ የደረሰልኝን
በመንገዴ ፡ ሁሌ ፡ የሚመራኝን
ሕይወቴንም ፡ ለቀየረልኝ
ቃልህ ፡ ብቻ ፡ ሁሌ ፡ አስተማማኝ

አዝ፦ ብዙ ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው
በቃልህም ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው
የደስታዬ/የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
መተኪያና ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x)

ቃልህን ፡ እወደዋለሁ (፪x)
ድምጽህን ፡ እወደዋለሁ (፪x)

ከአፍህ ፡ የሚወጣው ፡ ሕያው ፡ የአንተ ፡ ቃል
መሻት ፡ ግን ፡ ወደ ፡ እኛ ፡ ስቦ ፡ ያመጣል
ያድናል ፡ ይገላል ፡ ይተክላል ፡ ይነቅላል
እርሱ ፡ ያለው ፡ ብቻ ፡ በእርግጥም ፡ ይሆናል

ሳር ፡ ይደርቃል ፡ አበባው ፡ ይረግፋል
በምድር ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ይለዋወጣል
ዘመን ፡ ጊዜ ፡ የማይለዋውጠው
የአምላኬ ፡ ቃል ፡ ፀንቶ ፡ የሚኖር ፡ ነው

አዝ፦ ብዙ ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው
በቃልህም ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው
የደስታዬ/የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
መተኪያና ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x)

ቃልህን ፡ እወደዋለሁ (፪x)
ድምጽህን ፡ እወደዋለሁ (፪x)