ለእኔ ፡ ግን (Lenie Gen) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

የሚሰማ ፡ ግን ፡ በእርጋታ ፡ ይቀመጣል
ከመከራ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሥጋት ፡ ያርፋል
ጌታዬ ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x)
ብለሃል ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x)

አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x)

የሚያስፈልገው ፡ ጥቂት ፡ አንድ ፡ ነው (፪x)
በእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኖ ፡ አንተን ፡ ማድመጥ ፡ ነው (፪x)
ይህን ፡ ተረዳሁ ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x)
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ አደምጥሃለሁ (፪x)

አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x)

ከዝማሬዬ ፡ ይልቅ ፡ ኑሮዬ ፡ ያክብርህ (፪x)
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ስንቱን ፡ ላስጠራልህ (፪x)
ከአገልግሎቴ ፡ ይልቅ ፡ ሕይወቴ ፡ ያማረ ፡ ይሁን (፪x)
አንተ ፡ እንደምትወደው ፡ እንደፈቀድክ ፡ ይሁን (፪x)

አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x)

ጌታዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ (፪x)
ፊትህንም ፡ ማየት ፡ እጅግ ፡ ናፍቃለሁ (፪x)
የሚረዳኝ ፡ ፀጋ ፡ ከአንተ ፡ ፈልጋለሁ (፪x)
ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እቀርባለሁ (፪x)

የሚሰማ ፡ ግን ፡ በእርጋታ ፡ ይቀመጣል
ከመከራ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሥጋት ፡ ያርፋል
ጌታዬ ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x)
ብለሃል ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x)

አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x)